በበሰቃ ሀይቅ ዳርቻ በ80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ በልዩ የኪነ ህንፃ ጥበብ እንደተገነባ የሚነገርለት የመዝናኛ ስፍራ አገልግሎት መስጠት ሳይጀምር ለ8 ዓመታት ባለቤት አልባ ሆኖ በመቆየቱ መልሶ እየፈረሰ ነው ተባለ ።

ልዩ የመዝናኛ ስፍራው ከመተሀራ ከተማ በሶስት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በ143 ሔክታር መሬት ተከልሎ የተገነባ በመሆኑ ከሩቁ ለየት ብሎ ይታያል ።

በውጭ አገር ሰዎች የተገነባ ልዩ የመዝናኛ ስፍራ ነው ሲባል የሰማ እንጂ በእርግጠኝነት ዝርዝር መረጃ ያለው የከተማው ነዋሪ ማግኘትም አስቸጋሪ ነው ።

ስለሁኔታው ለማወቅ ጉጉት ያደረበት የኢዜአ የጋዜጠኞች ቡድን ከፈንታሌ ወረዳ ኢንቨስትመንትና ከወረዳው የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሁለት ባለሙያዎችን በመያዝ ወደ ቦታው ያቀና ሲሆን ግንባታው የሚደነቅ ብክነቱ ግን የሚያሳዝን ሆኖ አግኝቶታል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ወደ ቦታው ለመግባት ሜዳ ሜዳውን እየመረጡና ከፕሮሶፒስ እሾሃማ መጤ አረም ጋር እየታገሉ እንጂ መኪና ሲመላለስበት የነበረው የገጠር መንገድ አገልግሎት ሳይሰጥ ረጅም ጊዜ ስለሆነው ተመልሶ ጠፍቷል ።

በቦታው በበሰቃ ሀይቅ ዳርቻ እየዋኙ ከሚጫወቱ ጥቂት የአርብቶ አደር ህፃናት ልጆች በስተቀር አንድም የጥበቃ ሰራተኛ በስፍራው አልነበረም ።

የፈንታሌ ወረዳ ኢንቨስትመንት ፅህፈት ቤት ባለሙያ አቶ ከማል ዑመር እንደሚሉት ግንባታው በ80 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከ1999 ዓም እስከ 2003 ዓ.ም የተከናወነ ሲሆን ባለቤቱም ሶል ጆኦት ሳዑዲ አሜሪካን ኢንቨስትመንት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባኒያ በሚል የተመዘገበ ነው ።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የሳዑዲ አረቢያ ተወላጁ የኩባኒያው ባለቤት በ2003 ዓ.ም የበሰቃ ሀይቅ የውሃ መጠኑ ጨምሮ ወደ መዝናኛ ስፍራው በመግባት በግንባታው ላይ ጉዳት በማድረሱ ተበሳጭተው አካባቢውን ለቀው በመሄዳቸው ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅና አገልግሎት መስጠት ሳይጀምር መቅረቱን ባለሙያው ተናግረዋል ።

በጊዜ ሒደት ባለሃብቱ እዛው ሀገራቸው ላይ እንደሞቱ የተሰማ ሲሆን ህጋዊ ወራሾች የሆኑ ቤተሰቦቻቸው ስራውን ለማስቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው ከአንድ ወር በፊት ለመንግስት አሳውቀው እንደተፈቀደላችው አቶ ከማል አስረድተዋል ።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ግንባታው ከመቋረጡ በፊት አርብቶ አደሮችን ጨምሮ 300 ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ነበር ተብሏል ።

ወጣቱ ዓሳ አጥማጅ ዴቪድ ብርሃኑ በመዝናኛ ስፍራው የሚገኘውን አንዱን ማማ መኖሪያው አድርጎ እየተጠቀመበት መሆኑን ይገልፃል ።

ወጣቱ ተወልዶ ያደገው በመተሃራ ከተማ ቀበሌ 01 ሲሆን አሁን ግን ወደ ከተማ የሚወጣው ያጠመደውን የዓሳ ምርት ለመሸጥ እንጂ ውሎና አዳሩን በመዝናኛ ስፍራው ውስጥ አድርጓል ።

ምንጭ – ኢዜአ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *