የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሐጅ ሙሐመድ አሚን ጀማል ኃላፊነታቸውን አዲስ ለተቋቋመው የአሊሞች ምክር ቤት ሰብሳቢ ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር ኢድሪስ አስረከቡ። በመጅሊሰ ታሪክ የመጀመሪያው ሰላማዊ የሆነው የስልጣን ርክክብ በዛሬው እለት ነው የተካሄደው።

የስልጣን ርክክብ ሂደቱ አዲሱ የኡለማና የባላደራ ቦርድ ኮሚቴ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ በተገኙበት በሰላም መጠናቀቁም ተገልጿል።

የአሊሞች ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ እና የአንድነት ሀገር አቀፍ ስብሰባ ላይ ነበር የተመረጠው።

ከ300 በላይ ኡለማዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የተሳተፉበት ጉባዔው፥ 23 አባላት ያሉት ጊዜያዊ የኡላማዎች ምክር ቤት መምረጡም ይታወሳል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *