በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ 43 ሺህ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

43 ሺህ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ የተገኘው ተጠርጣሪ ግለሰብም ቡቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላሩ ሊያዝ የቻለው የአካባቢው ማህበረሰብ በቅርቡ ለሚገኙት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ጥቆማ በመስጠታቸው መሆኑንም አስታውቋል።

ጥቆማው የደረሳቸው የፌደራል ፖሊስ አባላትም በፍጥነት ተጠርጣሪውን በመያዝ ፍተሻ ባደረጉበት ወቅት 43 ሺህ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ ያገኙታል ማግኘታቸውንም ገልጿል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ረዳት ሳጅን ተመስገን ያምላክ እንደገለጹት፥ የተያዘው ህገ ወጥ ዶላር ሀሰተኛ መሆኑን ወደ ብሄራዊ ባንክ ተልኮ መረጋገጡን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅትም ተጠርጣሪው ህገ ወጥ ገንዘብ በማዘዋወርና ሃሰተኛ የዶላር ኖት በመያዝ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት በሂደት ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *