የሃይማኖት ግጭት ለማስነሳት የሚሰሩ የተደራጁና የተገዙ ሃይሎች መኖራቸው ተሰማ። ሰሞኑንን በአንዳንድ አካባቢዎች የተሞከረውና በቁትጥር ስር የዋለው ግጭትም የዚሁ አካል መሆኑ ተገለጸ። ጅማን በሃይማኖት ልዩነት ለማተራመስ እቅድ መያዙና እቅዱ እንደሚከሽፍ ተገለጸ። ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “በቀርቡ በሃይማኖት ሽፋን ደግሞ ይመጣሉ” ሲሉ አገሪቱን ለማሸበር ስለተነሱ ሃይሎች መናገራቸው ይታወሳል።

አሰላ በሃይማኖት ስም ተነስቶ ወዲያው በጥጥር ስር የዋለውን ግርግር አስመልክቶ አስተዳዳሪው ለኦኤም ኤን እንደተናገሩት ግርገሩ ሊከሰት የማይገባውና እዚህ ግባ የሚባል ችግር የታየበት አልነበረም። ሕዝቡ ይህንን ድርጊት ከጀርባ በሚነዷቸው ቡድኖች አማካይነት የፈጸሙትን ከመንግስት ጋር በመሆን ለህግ ለአቅረብ እየሰራ ነው ሁለተኛ አይደገምም ሲሉ ተናግረዋል። አንድ ሰው መሞቱንም አስታውቀዋል።

Related stories   የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርት

ይህንኑ  ዜና ተከትሎ ዝግጅት ክፍሉ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ጅማን ማዕከል ያደረገ የሃይማኖት ብጥብጥ ለማስነሳት ሴራ እየተሸረበ መሆኑንን ደርሰንበታል ብለዋል። በሌሎችም አካባቢዎች በተመሳሳይ ከሃይማኖት ጀርባ እሳት በመለኮስ የግጭቱ አትራፊ ለመሆን የሚሰሩ መኖራቸውን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት እላይ ታች የሚሉና የቀድሞ የስለላ መዋቅር ውስጥ የነበሩ ክፍሎች ተለይተው በቁትትር ስር ሊውሉ እንደሚገባ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። በተለይም ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩ መረጃዎችን በመርመር ህዝብረተሰቡ ራሱን ከአደጋ እንዲከላከልም ጥሪ አቅርበዋል።

Related stories   "ነጭ ቀለም ያላቸው የአረብ ወታደሮች በኢትዮ ሱዳን ድንበር እየሰፈሩ፣ አዳዲስ ከምፕ እየገነቡ ነው"

ከጀርባ በመሆን በሃይማኖትን ስም የፖለቲካ ጥቅም ለማግበስበስ የሚሰሩ አካላትን ሕዝብ ነቅቶ እንዲጠብቅ ጥሪ ያቀረቡት ወገኖች፣ በተገዛ አጀንዳ አገሪቱን ለማተራመስ፣ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የተደራጁ ተላላኪዎች ይህንኑ ዓላማቸውን ለምሳካት እንደማይተኙ ሁሉ ሌሎች ሰላማዊ ዜጎች አካባቢያቸውን ነቅተው እንዲጠብቁ ለማስቻል ስራ እንደሚሰራም አመላክተዋል።

አደገኛ አዝማሚያ ያላቸው ያላቸው መረጃዎችን ማጣራትና ምንጮቻቸውን መመርመር እንደሚያስፈልግ፣ ከስሜታዊነት በዘለለ በርጋታ ነገሮችን ማጤን እንደሚገባ ዝግጅት ጅፍሉ ያናገራቸው አስታወቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከወራት በፊት በአገሪቱ የተፈጠረውን ግጭት አስመልከተው ሲናገሩ ” በቅርቡ በሃይማኖት ስም ይመጣሉ” ሲሉ መናገራቸውና ሕዝቡ ራሱን እንዲጠብቅ መምከራቸው የሚታወሰ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *