የሸገር ገበታ ግንቦት 11 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ።

በእለቱም በመርሃ ግብሩ ላይ ለመካፈል መቀመጫ የገዙ አካላት ቤተ መንግስትን የሚጎበኙ ሲሆን፥ ምሽት ላይም በሚዘጋጀው የእራት ስነ ስርዓት ላይ እንደሚካፈሉም አስታውቀዋል።

የሸገር ገበታ ዓላማ በዋናነት የመብላትና የመጠጣት ሳይሆን፥ አሻራ የማኖር እና ታሪክ የመስራት መድረክ ነው ሲሉም አቶ ንጉሱ ተናግረዋል።

መርሃ ግብሩ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የአዲስ አበባን ወንዞች ዳርቻዎችን እና ሌሎች ተያያዥ መናፈሻዎችን ለማልማት ይፋ የተደረገውን ፕሮጀክት ለመደገፍ ገንዘብ ለማሳሰብ የተዘጋጀ ነው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በዚሁ 5 ሚለየን ብር ዋጋ የተቆረጠለት ገበታ ላይ ለመታደመም በርካታ ተቋማት፣ ኤምባሲዎች እና ግለሰቦች ፍላጎት በማሳየት ገንዘቡን ገቢ ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል።

በሸገር ገበታ መርሃ ግብር ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ አካላትም በቀሩት ጥቂት ጊዜያት ተጠቅመው በመመዝገብ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ንጉሱ አክለውም፥ የተለያዩ አካላት ፕሮጀክቱን በአድናቆት መመልከታቸውንና ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸውን የገለጹት አቶ ንጉሱ፥ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ኤምባሲዎች እና የልማት ተቋማት ፍላጎት አሳይተው ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

እስካሁንም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ድርጅት (ዩኤንዲፒ) እና በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማድ ድርጅት (ዩኒዶ) 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ 600 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም የጣሊያን መግስት 5 ሚለየን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን አንስተዋል።

በተጨማሪም የቻይና መንግስት ሸገርን የማስዋብ የወንዝ ዳር ፕሮጀክቱን ዲዛይን እና 12 ኪሎ ሜትር ስራ ሙሉ ወጪን ለመሸፈን ፍላጎት ማሳየቱንም አንስተዋል።

ነገር ግን ፕሮጀክቱ እውን የሚሆነው ኢትዮጵያውያን ሲሳተፉበት ነው ያሉት አቶ ንጉሱ፥ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእውቀት፣ በጉልበት፣ በገንዘብና በተለያዩ መንገዶች ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየታቸውን አያይዘው ገልፀዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

እስካሁን ባለው ጊዜም ከ200 በላይ ተቋማትና ግለሰቦች በገንዘብ ይሁን በተለያየ ደረጃ አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት ማሳየታቸውንም ነው አቶ ንጉሱ ያስታወቁት።

ሸገርን ማስዋብ ፕሮጅክት በሚል የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው።

ከተማዋን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ፥ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል።

ፕሮጀክቱ በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

በሙለታ መንገሻ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *