“Our true nationality is mankind.”H.G.

ቶሞካ ቡና እየተዘረፈ ነው፤ ተስተናጋጆች ተባባሪ ናቸው

አቶ ዘላለም ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ነው። ከዓመታት በሁዋላ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ወደ ሃላፊነት መምጣት ተከትሎ በተፈጠረው አጋጣሚ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ይናገራሉ። በአዲስ አበባ ቆይታቸው ለጊዜው ባረፉበት መኖሪያቸው አቅራቢያ ካለው ቶሞካ ኪዮስክ የቡና ደንበኛ ሆነው ከርመዋል። ቶሞካን እንደምሳሌ ቢያነሱም አጠቃላይ ኢትዮጵያን እየናጣት ያለው ሃላፊነት የማይሰማቸው ወገኖች ተግባር መሆኑንን የገልጻሉ። ይህ ማህበራዊ ቀውስ አገሪቱን እንደሚደፍቃትም ያምናሉ።

በአዲስ አበባ በተዛወሩባቸው ስፍራዎች በሚያስተውሏቸው ጉዳዮች እጅግ መደንገጣቸውን ያወሱት አቶ ዘላለም፣ በሚኖሩበት አሜሪካ ተወልዳ ያደገችው ልጃቸው በአጭር ቀን ትዝብቷ የሰጠቻቸው አስተያየት አስደንግጧቸዋል። ልጃቸው ” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስተዋል፣ ከተማቸውን ለጥቂቶች በሃላፊነት ሰጥተው ተኝተዋል። በግል ሃላፊነታቸውን አይወጡም። ግድ የለሽና ዳተኛ ናቸው ” ነበር ያለቻቸው።

አቶ ዘላለም ለዛጎል የአሜሪካ ተባባሪ እንደነገሩት ልጃቸው ላነሳቸው ሃሳብ ቶሞካ ቡና ማሳያ ነው። በሁሉም የቶሞካ ኪዎስኮች ተፈጻሚ መሆኑንን ባያረጋግጡም እሳቸው ጊዚያዊ ደንበኛ በሆኑበት ቡና መቸርቸሪያ ያጋጠማቸውን ለማመን ተቸግረዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ ጉዳዩ ቀላል ቢመስልም አገሪቱ የገባችበትን የማህበራዊ ቀውስ /ግሽበት ግን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ነገሩ እንዲህ ነው። አቶ ዘላለም በየቀኑ ቶሞካን ይሳለማሉ። አንዴ፣ ሁለቴ ወይም ከዚያ በላይ። እናም ቡና ካዘዙ በሁዋላ ክፍያ ፈጽመው የሚሰጣቸው ደረሰኝ አስገራሚ ነው። አንድ ቡና አዘው የሚሰጣቸው የአራት ቡና፣ የሶስት ቡና፣ ወይም እሳቸው ካዘዙት በላይ የሆነ ነው።

ጉዳዩ ሲደጋገም አስተናግጂቷን አንድ ቀን ለብቻ ሳብ አድርገው የሰበሰቡትን ደረሰኝ በማሳየት ማብራሪያ ይጠይቃሉ። አስተናጋጇም ጉዳዩ በሁለቱ እንደሚቀር ተማጽና ” ደሞዛችን ትንሽ ስለሆነ ከባሪስታው ጋር በመነጋገር በአንድ ደረሰኝ ደገመን ደጋግመን አዲስ ቲኬት ሳናስቆርጥ ሂሳቡን ኪሳችን እያስገባን እንሰራለን” ስትል መልስ ሰጠች።

ፈገግ በማለት ጥያቄያቸውን በማስከተል ” ታዲያ በዚህ መንገድ ምን ያህል ታገኛላቹህ” ሲሉ በአግራሞት አቶ ዘላለም ይጠይቃሉ። አስተናጋጅ ” ከባሪስታው ጋር በቀን አንድ አነድ ሺህ ይዘን እንወጣለን” አለች። አቶ ዘላለም ምክር ቢጤ ለግሰውና አመስግነው አስተናግጅን ተሰናበቱ።

በአንድ ሰንበት አስተናግጅት ቆንጆ መኪና እያሸከረከረሽ መጥታ አንድ ሱፐር ማርኬት ስትገባ አቶ ዘላለም አይዋት። የነገረቻቸው የሌብነት ታሪክ አረጋገጠችላቸው። እናም እንዲህ ያለው ማህበራዊ ቀውስ ባለበት አገር ለውጥ እንዴት ይታሰባል የሚለው ጉዳይ  አናታቸውን አዞረው።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ይህ በአንድ ቡና መቸረቸሪያ ኪዮስክ ውስጥ በየቀኑ የሚካሄደው ሌብነት የሚያስፈጽሙት ተገልጋዮች ናቸው። ይህ ” ምን አገባኝ” የሚል አስተሳሰብ ውጤት ነው። አገሪቱ በጥቅሉ በምን አገባኝ ባዮች ሳቢያ ለጥቂቶች የተሰጠች ለመሆኑ እንደ አንድ ማሳያ እንደሚመለከቱት ያስታወቁት አቶ ዘላለም ” ሰዎች የከፈሉትን ገንዘብ እና ያዘዙትን የማይገልጽ፣ ቀኑ የተዛባ ሃሰተኛ ደረሰኝ ሲሰጣቸው፣ ይህ ደግሞ በተደጋጋሚ ሲደረግ ዝም ማለት ከሃላፊነት ማነስ፣ ከግዴለሽነት የሚመነጭ አደገኛ ቀውስ ማሳያ ነው”

ሌሎችን የሚወቅሱት አቶ ዘላለም እሳቸው ይህንን የጠራራ ሌብነት አስመልክቶ ምን እንዳደረጉ ተይቀው ” ሲደጋገምብኝ ደረሰኝቹን ሰብስቤ ሃላፊ ነው ለሚባል ሰው ሰጥቻለሁ። ከዛ በላይ መሄድ አልችልም” ብለዋል። ባለ ድርጅቶች ከሚያገኙት ትርፍ አንሳር ተመጣጣኝ ክፍያ ሊከፍሉና ጥቅማ ጥቅም በመስጠት ሰራተኞች እምነት የሚጣልባቸው እንዲሆንና ድርጅቱ የራሳቸው እንደሆነ አድርገው እንዲያስቡ ማድረግ እንደሚገባቸው  አቶ ዘላለም ሃሳብ ሰጥተዋል።

ዋናው መተኮር ያለበት ” ምን ያገባኛል” የሚለው ያልሰለጠነ አስተሳሰብ ላይ ማተኮር እንደሆነ የተናገሩት አቶ ዘላለም፣ ዜጎች በማንኛውም ጉዳይ ላይ ህግን ተንተረሰው በሃላፊነት የበኩላቸውን ካላበረከቱ አገር ከቀውስ አትወጣም። አሁን አገሪቱን ከገጠማት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስ በላይ ማህበራዊ ቀውሱ እጅጉኑ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

አገሪቱን ወደ ቀውስ የሚመሩ እጅግ ጥቂት ሰዎች እንዳሻቸው የሚፈነጩት ከዚሁ ምን አገባኝ ከሚል የአብዛኞች እምነት የተነሳ ነው። አብዛኞች ምን አገባኝ በሚል የጨለማ ጎዳና መጓዝ ሲመርጡ አፈ ጮሌዎችና ደፋሮች ይነግሳሉ። ካለው አጠቃላይ የግንዛቤና የስልጣኔ ችግር ጋር ተዳምሮ የጥቂቶች ፍላጎት አገሪቱን ይንጣታል። አሁን እየሆነ ያለውም ይህ ነው።

በተለያዩ አገራት በአብዛኛው ህዝብ የአገሩ ህግ አስጠባቂ፣ የአገሩ ዘብ፣ የአገሩ ተንከባካቢ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ዘላለም ፣ የእነዚህ አገራት ህዝብ ውስጥ ወምጀል የሚሰሩ ቢኖሩም እንደ ኢትዮጵያ ምን አገባኝ ከሚል የቸልተኛነት መንፈስ እንዳልሆነ ይናገራሉ።

“አንድ ቀነ በመስኮት እቃ ሳስገባ ጎረቤቴ ስልክ ደውላ ፖሊስ ጠራችብኝ” ያሉት አቶ ዘላለም፣ በኢትዮጵያ በዝምታ የተዋጡና ምን አገባኝ በሚል ስሜት የታነቁ ዜጎች ዝምታቸውንና ዳተኛነታቸውን ሊሰብሩ ይገባል” ብለዋል።

ምስል – ከቶሞካ ኪዮስኮች አንዱ ሲሆን ከታሪኩ ጋር በተለይ አይገናኝም

 

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0