የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቅዳሜ እና እሁድ ባካሄደው ኦፕሬሽን በመዲናዋ የተለያዩ ወንጀሎችን በተደራጀ መልኩ ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን እና ለወንጀል ተግባር ሲውሉ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ፖሊስ በልደታ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ ክፍለ ከተማዎች ባካሄደው ጥናት ላይ በተመሰረተ ዘመቻ እና ድንገተኛ ፍተሻ ሰነድ ሳይኖራቸው እና ህጋዊነታቸው ያልተረጋገጡ 260 ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

በህገ ወጥ ተግባር ላይም ማለትም በቅሚያ፣ በዝርፊያ፣ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና መድሃኒት ዝወውር ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በተጨማሪም ከአደገኛ እፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ትልልቅ ሆቴሎች የሚያርፍ የውጭ ሀገራት ዜጎችን በደላላ እና በሆቴል ሰራተኞች በኩል በማግባባት ሺሻ እና ባእድ ነገር ተቀላቅሎ ወደ ሚጨስባቸው ስፍራዎች በመውሰድ የወንጀል ድርጊት እንዲፈፀምባቸው ያደረጉ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ምክትል ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

በቅንጅት የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ከ250 ሺህ ብር በላይ ትልልቅ ህንፃዎችን በመከራየት የወንጀል ድርጊት ሲፈፅሙ እንደነበርም አመልክተዋል።

በሶስት ክፍለ ከተሞች በተደረጉ ዘመቻዎች ከ2 ሺህ 500 በላይ የሺሻ ማጨሻና እና መገልገያዎች ከዋና ዋና የድርጊቱ ፈፃሚዎች ጋር ተይዘዋል። ግማሽ ኪሎ የሚደርስ አደገኛ እፅም በዘመቻው ተይዛል። ፖሊስ ሺሻ ሲያጨሱ የተገኙ በርካታ ግለሰቦችን በመምከር እንደለቀቀም ነው የተመለከተው።

በመግለጫው ምን ያህል ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ አልተገለፀም።

በበላይ ተስፋዬ – FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *