“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ልዩ የድንጋይና የአለት ዘይት” ዜና ከሰላሳ ዓመት በፊት ይታወቃል፤ “… የሕዝብን ልብ ትርታ ለመጨመር ጥረት ባይደረግ “

ድንጋይና አለቶችን ሰባብሮ በማቅለጥ ነዳጅ ማግኘት የሚያስችል ሃብት መገኘቱ እንደተረጋገጠ የትግራይ ክልል መሪ ማስታወቃቸውን ተከትሎ የፌደራሉ የማዕድን፣ የፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር ቀጸላ ታደሰ ልዩ የተባለው ነዳጅ ስለመኖሩ እንዳልተደረሰበት አስታወቀዋል። THE FINFINNE INTERCEPT ይህንኑ ጉዳይ አስመለክቶ  ልዩ መረጃ እንዳለው አመልክቷል።

ጉዳዩን አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት ዶ/ር ቀጸላ ታደሰ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የነዳጅ ዘይት ክምችት እንደሚገኝ የሚያመላክቱ ጥናቶች መኖራቸውን ጠቁመው፣ አሁን በትግራይ ክልል ሼል ኦይል ተገኘ ስለመባሉ “ይህ መግለጫ ተጨባጭና አስተማማኝ የሚሆነው የቁፋሮ ሥራና በቤተሙከራው ውጤቶች ተደግፎ ሲቀርብ ነው” እንደሆነ ለቢቢሲ አማርኛው ዝግጅት ክፍል ተናግረዋል።

ዶክተር ደብረጺዮን አያይዘውም፥ በትግራይ ክልል እምባ አላጀ፣ ነበለት እና  ዓዲ-ግራት ባሉት ተራራማ አካባቢዎች በአይነቱ ልዩ የሆነ ነዳጅ መኖሩ በጥናት መረጋገጡን አስታውቀዋል። ይህም በአካባቢው የሚገኙ ድንጋይና አለቶችን ሰባብሮ በማቅለጥ የሚገኝ እንደሆነና ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንደሚጠይቅ አክለዋል።

የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታምሩ መርሻ በበኩላቸው ከሰላሳ ዓመታት በፊት በተለያዩ አካባቢዎች የተለያየ መጠን ያለው የነዳጅ ክምችት እንደሚኖር ከሌሎች አገራት ኩባንያዎች ጋር በመሆን ጥናት ተካሂዶ እንደነበር ያስታውሳሉ። አያይዘውም  በዚህ ከሰላሳ ዓመት በፊት በተጠና ጥናት ከፍተኛ ክምችት የሚገኝበት የኦጋዴን ቤንዚን ፣ አባይ ሸለቆ፣ በስምጥ ሸለቆ (ከአፋር እስከ ደቡብ ኦሞ)፣ በጋምቤላ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በመቀሌ እና መተማ ተፋሰስ የተለያየ መጠን ያለው የነዳጅ ክምችት መኖሩን ጥናቶችን ዋቢ አድርገው በጥቅሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። የተገኘ ልዩ ነገር ካለም ለመተማመን በላቦራቶሪ ተረጋግጦ ሲቀርብ ለመተማመን እንደሚያመች ተናግረዋል። አይይዘውም “ባይጋነን ጥሩ ነው፤ ተጨባጭ ነገር ሲኖር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግልፅ የሆነ መግለጫ ይሰጣል፤ የሕዝብን ልብ ትርታ ለመጨመር ጥረት ባይደረግ ” ሲሉ መክረዋል።

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

THE FINFINNE INTERCEPT መረጃ እንዳለው ጠቅሶ  እንዳለው ዶ/ር ዮሓንስ ይህደጎ የተባሉ በአውስትራሊያ የሚገኝኙ የስነምድር ተመራማሪ/ ሳይንቲስት ከሌሎች የአውስትራሊያ የዘርፉ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በትግራይ የ oil shale reserve መኖሩን አረጋግጠው የ mining plan ሁሉ ማዘጋጀታቸውን ጽፏል።ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደተጀመረም ምንጮች ነግረውናል። ሲል የዶክተር ደብረጽዮንን ዜና ያጠናክራል። 

ይሄን ጉዳይ በቅርበት ከሚከታተሉት ውስጥ የክልሉ ምክትል ር/መ ዶ/ር ደብረጺዮን ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር አክሊሉ ሃይለሚካኤል፤ እና የኤፈርት ዋና ስራ አስፈፃሚው በየነ መክሩ እንደሚገኙበት ፊፊኔ ኢንተርሴፕት ጥቁሟል።

በህገ መንግስቱ መሰረት ይላል ፊፊኔ ኢንተርሴፕት ፣ እንደዚህ አይነት ሃብቶች የፌዴራል መንግስቱና የክልሉ መንግስት የሚጋሩት ነው። ይሁን እንጂ ይትግራይ ክልል ከፌደራል መንግስቱ የተደበቀ ስራ እየሰራ ስለመገኘቱ የኢሜል ልውውጦች በማስረጃነት በማሳየት ወቅሷል። ክልሉ የተፈጥሮ ሃብቱን ለመጠቀም እቅድ ነድፎ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ እየሰራ መሆኑንን በማሳየት የህግ ጥያቄ አንስቷል።

የትግራይ ክልል ስለህግ ጥሰቱ በይፋ የሰጠው ምላሽ ባይኖርም ፊፊኔ ኢንተርሴፕት ብዝሰፈረው ዘገባ ስር Samuel Kebede የተባሉ አስተያየት ሰጪ ዜናው የሚጋነነ እንዳልሆነ፣ የተጠቀሰው የሺል ዘይት በትግራይ ክልል መገኘቱ ሚስጢር አስቀድሞ ከረዥም ጊዜ በፊት የሚታወቅ መሆኑንን፣ ሃብቱ ከተለመደው የዘይት ክምችት የተለየ መሆኑንን ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ይህንን ሃብት ለመጠቀም እጅግ ከፍተኛ ውጪ / ኢንቨስትመንት/ እንደሚጠይቅና ጥቅም ላይ ሲውል የአካባቢ ውድመት እንደሚያስከትል ጠቁመዋል። ከዚህም አንጻር እሳቸው እንደሚያምኑት ዜናውን ክልሉ ሆን ብሎ የወጣቶችን ስነልቡና ለማነሳሳትና ለፖለቲካ ፍጆታ አድርጎ ሊጠቅምበት እንዳሰበ ገልጸዋል።

This is not a big deal. The occurrence of oil shale in Tigray has been known for long time. Oil shale is not the best kind of resource for oil production. This is different from conventional oil reserve. Production of oil from oil shale involves costy financial investment as well as environmental damage. At this level, I believe, Tigray State can only use this as a political resource than economic one. They may use it to uplift the moral of the youth.

ቢቢሲ ማዕድን ሚኒስቴርን አነጋግሮ ባቀረበው ሪፖርት የሚከተለውን ጥናት አጣቅሷል።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

በአውሮፓውያኑ 2018 ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲና ተቋማት የተውጣጡ የአጥኝዎች ቡድን ‘Economic geology value of oil shale deposits: Ethiopia Tigray and Jordan’ በሚል ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሁፋቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሼል ኦይል ክምችት እንደሚገኝ ፅፈዋል። ከእነዚህ ቦታዎች አንዱ ትግራይ ክልል፤ ከፍተኛ የሆነ የሼል ኦይል ክምችት እንደሚገኝበትም በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ ተመላክቷል።

በጥናቱ እንደተገለፀው ይህ የነዳጅ ዘይትም ብዙውን የክልሉን ቦታ የሚሸፍነውን – በአዲግራት አሸዋማ አለት ሥር በስፋት የተሰራጨ ነው። በመሆኑም ብዘት፣ ዕዳጋ ዓርቢ፣ ነበለት እና አጽቢ የሚባሉ አካባቢዎች መገኘቱንም ጥናቱ አትቷል። በትግራይ ክልል ይገኛል የተባለው የነዳጅ ክምችትም ወደ 3.89 ቢሊየን ቶን የሚጠጋ እንደሆነ በጥናታቸው አመላክተዋል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኘው የኦይል ሼል ክምችትም ከ55-60 በመቶው የካርቦን ይዘት እንዳላቸው ጥናቱ በዝርዝር አስቀምጧል።

በዓለም ላይ የተለያዩ የነዳጅ አይነቶች ያሉ ሲሆን የሼል ኦይል የአለት ዓይነቱ በተለያዩ ዘዴዎች በመሰነጣጠቅና ጋዝ እንዲያመነጭ በማድረግ የሚመረት የተፈጥሮ ጋዝ ዓይነት ነው። በሰሜን አሜሪካ የሼል ኦይል በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል።

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0