ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኡጋንዳ በር ልትዘጋ ነው፤ እዛ የመሸጉ አተራማሾች ተላፈው እንዲሰጡ መግባባት እየተደረሰ ነው!!

የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ወደ ኬንያ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ ወደ ዩጋንዳ አምርተው ነበር። የሁለቱም መሪዎች ድንገተኛ ጉብኝት ከድንበር አካባቢ ጸጥታና ሰላም ጋር ግንኙነት እንዳለው በጨረፍታ ቢገለጽም ዝርዝር ጉዳዮች አልቀረቡም። በተለይም አቶ ደመቀ ዩጋንዳ የቆዩበት ጉዳይ ብዙም አልተባለለትም።

የዛጎል መረጃ አቀባዮች እንደሚሉት ግን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩጋንዳ ጉዞና የጠቅላይ ሚንስትር አብይ መልዕክት ዩጋንዳ ድንበር ላይ ራሳቸውን ለጦርነት የሚያዘጋጁና ድርጅት የፈጠሩ ሃይሎችን አስምለክቶ ነበር። ከደቡብ ሱዳን እና ከኬንያ የሚነሱት ሃይሎች የሚያደራጃቸው አካል በመኖሩ በዚህ ጉዳይ ነው ጉዞው ያስፈለገው።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

በዩጋንዳ መንግስት እውቅና አግኝተው የሚኖሩ ሃይል የሚያደራጁ አካላት መኖራቸውን ጠቅሶ መንግስት በማስረጃ ድርጊቱን ለማስቆምና ከምንጩ ለማድረቅ እንዲቻል ሙሴቪኒ ተባባሪ እንዲሆኑ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

በዩጋንዳ ድንበር ማሰልጠኛ ግንብተው የሚንቀሳቀሱና ከዛ እየተወረወሩ  አገር የማወክ ተግባር የሚፈጽሙ አካላትን የሚያደራጁት ክፍሎች መንግስት ተላልፈው እንዲሰጡት መጠየቁን፣ የዩጋንዳ መንግስትም ተባባሪ ለመሆን መስማማቱን የዜናው ምንጮች አስታውቀዋል።

በዩጋንዳ የከተሙትን አመራሮችና አሰልጣኞች ስም ለጊዜው ለምጥቀስ ያልፈለጉት ምንጮች ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኬንያ ላይ ከደረጉት ስምምነት ጋር ተጎዳኝቶ ሽፍቶቹን በጋራ የመድምሰስ፣ የመቃረም ስራ በቅርቡ እንደሚሰራ ነው ምንጮቹ ያመለክቱት። በሞያሌ በኩል ኬንያ ድንበሯን በመቆጣጠሩዋ የነበረው ሁከት መቋጨቱን ያወሱት እነዚሁ ክፍሎች በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች ከደቡብ ሱዳን ጭምር እየተንደረደሩ ጥፋት በሚፈጽሙና አልፎ አልፎ የሚታየውን ሁከት በተመሳሳይ ለማክሰም እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

በድቡብ ሱዳን እነማን በዚህ ተግባር ከማን ጋር ተባባሪ ሆነው እንደሚሰሩ መንግስት መረጃ እንዳልውና በጥብቅ እንደሚከታተለው ያወሱት የዛጎል ምንጮች፣ የሱዳን፣ የኬንያና የኢትዮጵያ በጥምረት መስራት ለተጠቀሱት ክፍሎች ስጋት እንደሆነም ተመክቷል።

በዩጋንዳ አንዳንድ አኩራፊ ፖለቲከኞችና የሚፈለጉ ሃይሎች ሰላማዊ መስለው መመሸጋቸውን፣ አንዳንድ በከፍተኛ ንግድ ስራ የተሰማሩ መሆናቸውን መንግስት እንዳረጋገጠ የዜናው ሰዎች አክለው ጠቁመዋል። ለውጡ ይፋ ከሆነ ወዲህ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የተባለ የሪፎርምና የማብቃትና ስራ በሚሊታሪ ልምዳቸው ከታወቁ አገራት ጋር መከናወኑና እየተከናወነ መሆኑን ይታወሳል።

0Shares
0
Read previous post:
አዛውንቱ ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም በአዲስ አባ ጎዳና – ከሹፌሩ ማስታወሻ

የአስጎብኚ ድርጅት ሹፌር ነኝ፡፡ አለቃዬ አንድ ጥቁር እንግዳ በአ.አ ጎዳናዎች እንዳንሸራሽር አዘዘኝ፡፡ ጓድ መንግሥቱ በድብቅ...

Close