“…. ሰሞኑን ወደ አስመራ እሄዳለሁ።የአርበ ኞችን አጽም ለማስመጣት።አጠቃላይ 68 አርበኞች አጽም ነው ያለው። ከነዚህ ውስጥ ግንቦት ሰባት -ከአርበኞች ግንባር ጋር ከተዋሀደ ወዲህ የሞቱት ሦስቱ ብቻ ናቸው።ሁለቱ በህመም፣አንዱ በአደጋ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ።65ቱ የሞቱት አርበኞች ግንባር የሚባለው ድርጅት በነበረ ጊዜ ነው።

አብዛኞቹን የገደላቸውም ራሱ አርበኞች ግንባር ነው። ከ እነዚህም መካከል በወሎ ረሀብ ወቅት እንግሊዞች ፡አዳፕት” ያደረጉት እና ለትግል ከእንግሊዝ ወደ በረሃ የሄደ ዜግነቱ እንግሊዛዊ የሆነ ልጅ አለ። አሟሟቱ እጅግ ያሳዝናል። በቁመቱ ልክ ጉድጓድ ቆፍረው ካስገቡት በኋላ በረሀብ ቀጥተው ነው አፈር ያለበሱት።

ከ65ቱ ውስጥ በህመም የሞቱት ከሦስት እና አራት አይበልጡም። የተቀሩትን በተለያዩ ሰበቦች አርበኞች ግንባር ነው የገደላቸው። የእነዚህን ወገኖች አጽም ነው ኃላፊነት ወስጄ እያሰባሰብኩ ያለኹት። ዛሬ በየፌስ ቡኩ ስለ አጽም ፣ስለ ሠራዊቱ ጉዳይ አሉባልታ የሚጽፉት፤ እነዚህን ሰዎች በመግደል እጃቸው ያለበት ሰዎች ናቸው። አልፎ አልፎ በአማራ ክልል ቴሌቪዥን ተደርድረው የማያቸው አንዳንድ ሰዎች ከእንግሊዝ ሀገር የሄደውን ልጅ በአሳዛኝ ሁኔታ የገደሉ ናቸው።

እንደ ንጹህ ሰው የሚዲያ ሽፋን ተሰጥቷቸው ሚዲያ ላይ ወጥተው ሲያወሩ ዐይቻቸዋለሁ። እስካሁን ድርጅት ውስጥ ስለነበርኩ ይህን ነገር ለመናገር ፈቃደኛ አልነበርኩም። ዛሬ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሌሎችም አሉ።እዛ ቦታ የሄዱ ታጋዮችን ከመግደል አንስቶ እጅ እና እግራቸው መንቀሳቀስ እስከማይችል ደረስ “ፓራላይዝ” ያደረጉ ወንጀለኞች በነጻነት እየተንቀሳቀሱ ነው። እነዚህን ወንጀለኞች የክልሉ መንግስትም ያውቃቸዋል።
ከዚህ ከተማ ለትግል የሄደን ተስፋ የሚባል አንድ መሀንዲስ ሚስቱን አስገድደው ቤቱን 600 ሺህ ብር ካሸጡ በኋላ እሱን ገድለውታል።ሚስቱ ይህን ብሶትና ሀዘኗን አምቃ አማራ ክልል ድረስ ሄዳ አቤት ብላለች። እነዚህ ናቸው ዛሬ በፌስቡክ ብዙ እያወሩ ያሉት….” ሙሉውን አባይ ሚዲያ ላይ ስሙት።

(የክልሉ መንግስት በዋቢነት ስለተጠቀሰ ማsተባበያ አያስፈልገውም)

Samson Michailovich

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *