May 9, 2021

ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

በተጭበረበረ ማንነት መምህራንን ለማሳመጽ የወሬ ውፍጮዎች የሚበትኑትን መረጃ ማህበሩአወገዘ፤ አጋልጣለሁ ብሏል

ከህክምና ባለሟዎች ጀርባ በመሆን የተጀመረው የማተራመስ እቅድ ሲከሽፍ አሁን ደግሞ ወደ መምህራን የዞረ ይመስላል። ለውጡን በችግርና በአመጽ በመተብተብ መንግስት ስራውን እንዳይሰራ ያቀደውና መልኩን እየቀያየረ የሚነሳው ሁከት ያደረሰው ጉዳት በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም። በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኩ አገሪቱን ጎድቷል። ዜጎች ላይ የተፈጸመው የሴራ ፖለቲካው ውጤት የሆነው ማፈናቀልና መንጋን እያሰማሩ አገር ማተራመስ መኩን እንዳይዝ አሁንም ጥረቱ አልቆመም። የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ይህንን የተረዳ ይመስላል የሚክተለውን ጥሪ አሰምቷል።


የተከበራችሁ የከተማችን መምህራን ካሁን በፊት እንደገለፅነው የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር የመምህራንን ጥያቄ ልክ እንዳሁን ቀደም ሁሉ ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻል እንዲሁም ምላሽ መስጠት ያለበት የመንግስት አካል ቃል በገባው መሰረት ጥያቄዎቻችንን ሳይመልስ በመዘግየቱን በትናንትናው እለት ማለትም በቀን 15/09/2011ዓ.ም ከክፍለ ከትሞች ሰብሳቢዎች ጋር ባደረግነው ምክክር ስብሰባ በመገምገም የጋራ አድርገን በቀጣዩ ሳምንት አስቸኳይ የምክር ቤት ስብሰባ በወቅታዊ የመምህራን ጉዳይ ላይ ለመምከር ስብሰባ ለማካሄድ ወስነናል።

በተለይ የአ/አ መምህራን ማህበር ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በምክር ቤት ስብሰባ ተወያይቶ አቋም በመያዝ ለሚመለከተው አካላት ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ልክ አንዳንድ የፌስቡክ ህቡዕ ቡድኖች ጥያቄዎቻችንን እነርሱ እንዳነሱት በማድረግ የማህበሩን ስም በማጠልሸት መምህራንን የመከፋፈል ስራ በተለያዩ የፌስቡክ የሃሰት ገፆች እለት ከእለት እየተሰራጨ ይገኛል (ስለነዚህ ገፆች ዝርዝር በቅርብ የምናወጣው መረጃም አለ)።

በተለይ እራሳቸውን ህጋዊ በማስመሰል ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ በማለት ጉዳዩን የማያውቁ መምህራንን ያልተፈለገ ዋጋ እንዲከፍሉና እሳት ውስጥ ለመጨመር እየተሰራ ስለሆነ እኛም በቀን 22/09/2011ዓ.ም እንደከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት መክረን ጥበብ በተሞላበት ለጥያቄዎቻችን ስትራቴጂ በመንደፍ ቅደም ተከተል አበጅተን ውሳኔ በምክር ቤት ካሳለፍን በሃላ ስለቀጣይ እርምጃችን የምናሳውቅ መሆኑን ተረድተን ከሃሰትኛ የፌስቡክ ገፆች መልዕክቶች እራሳችንን እንድንጥብቅ እያሳሰብን ምክር ቤታችን ስብሰባውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ በማንኛውም ፍቃድ ባላገኘ እና እነማን እንደሚመሩት በማይታወቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ባለመሳተፍ እንድትተባበሩንና ውሳኔያችንን በቅርብ የምናሳውቅ ስለሆነ እንዲሁም ህጋዊ መንገድ ተከትለን ጠቅላላ ጉባኤም ይሁን ሳላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በምክር ቤት አቅጣጫ መሰረት ብቻ መመራት እንደሚገባን ግንዛቤ እንድትይዙልን መላ የአዲስ አበባ መምህራንን እንጠይቃለን።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች በተለይ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ እና መሰል ስያሜን በያዙ የመምህራን ተወካይ በመምሰል ሃሰተኛ የፌስቡክ ገፅ እየተላለፉ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች እለት ከእለት እንደአሸን እየፈሉ መምጣታቸውን በመምህራን መካከል ውዥንብር በመፍጠር ሰላማዊውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማወክ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን መገንዘብ ችለናል ከዚህም ባለፈ ሰፊውን የከተማችንን መምህራን የማይመጥን እና የማይወክል አፀያፊ ቃላት በመጠቀም መልዕክት በማስተላለፍ፤ የተሳሳቱ ሃሰተኛ መረጃዎችን በመለጠፍ የመምህርነትን ሙያ እንዲራከስ፣ የግለሰብ ስምን በማንሳት መሳደብና ማጥጥላላት እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የኛን የመምህራንን ሙያ ክብር እና ስብእና የማይመጥንና የማይወክል መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። በርግጥ በመምህራን የተጠየቁ በርካታ ጥያቄዎችን እንደ ሽፋን በመጠቀም ማህበራችን የሰራቸውን በርካታ ተግባራት ነጥቆ በህገወጥ መንገድ ኮሚቴ አቋቁመናል እየተባለ ለስልጣን ሽሚያ በመምህሩ ስም በሰፊው እየተነገደ እንደሆነ በተለይ በተለይ የመምህራንን ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄዎች እንደሽፋን መጠቀም ዋነኛ መንገዳቸው ሆኗል። ሰለሆነም ከነዚህ ሃሳዊ የማህበራዊ ቡድኖች እራሳችን ከስሜት ፀድተን እንድንጠብቅ እያሳሰብን የምክር ቤት ስብሰባችንን አቋም የዛሬ ሳምንት የምናሳውቅ መሆኑን እናሳውቃለን።

ግንቦት 16/2011ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ
0Shares
0
Read previous post:
ለዝርፊያ፣ ለህገወጥ መሳሪያ ዝውውር፣ ለግድያ የተሰማሩ ከሰማኒያ በላይ ተሽከርካሪዎች ከየጦር መሳሪያ ጋር ተያዙ

ባህር ዳር ነዋሪዎች በስጋት ከሚኖሩባቸው ከተሞች አንዷ ናት። በዚህ መነሻ ከህዝብ በተገኘ ጥጥቆማ መነሻ የከተማው...

Close