ዘጠኝ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድነት ብሄራዊ ግንባር የሚል ፖርቲ በመመስረት ተዋሀዱ

 ዘጠኝ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ አንድነት ብሄራዊ ግንባር የሚል ፖርቲ በመመስረት መወሃዳቸውን አስታወቁ፡፡ የተዋሃዱት ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጲያ ብሄራዊ አንድነት ኮንግረስ፣ የኢትዮጲያ ህብር – ህዝብ ብሄራዊ ንቅናቄ፣ የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ህብረት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኮንግረስ፣ የጋንቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የጋንቤላ ህዝብ ፍትህ፣ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ፣ ሼኮና አካባቢው ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና የአርጎባ ብሄረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው፡፡

Image may contain: one or more people and people standing

ግንባሩ ሰላማዊ የትግል ስልትን በመቀየስ አዲስ እና የተሻለ ሊያሰራ የሚችል ጠንካራ የትግል ትብብር መስርቶ በህብረት መስራትን ዓላማ አድርጎ የተዋሀደ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይሄንን ግንባር ለመምራት ዋናና ምክትል አስተባባሪዎች፣ፀሀፊና ሁለት አባላት በድምሩ አምስት አባላት ያሉት ጊዜያዊ ኮሚቴ ተሰይሟል፡፡

ግንባሩን የመሰረቱ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች የጋራ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም የጋራ የአቋም መግለጫም አውጥተዋል፡፡ በቀጣይም ከግንባሩ ጋር ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ የሆነ አላማና ፕሮግራም ያለው ማንኛውም ፓርቲ ተቀላቅሎ በጋራ እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የፋይናስ ስርዓቱን በማይከተሉ ተቋማት ላይ ክስ እንዲመሰረት ወሰነ። 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፋይናስና ግዥና ደንብ ስርዓትን ተከትሎ በማይሰሩ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ ክስ እንደሚሰረት የሚስችል ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው ተመላሽ መደረግ ያለበትን የመንግስት ሃብት በማይመልሱ እና ቤት የፋይናስና ግዥና ደንብ ስርዓትን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲት መስሪያ ባቀረበው ሀሳብ መሰረት ክስ እንዲመሰረት ውስኗል፡፡ በኦዲት ግኝት ጉድለት የተገኘባቸው እና ለከተማዋ ዋና ኦዲተር መስርያ ቤት ምላሽ ያልሰጡ 53 ተቋማት ናቸው በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ውሳኔ የተላለፈው፡፡ ምክር ቤት 23 የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን እና 5 የይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኞችን ሹመት አፀደቀ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ባካሄደው ጉባኤ የተለያዩ ተቋማትን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀምን ተመልክቷል፡፡

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

ዶ/ር አምባቸው ከአማራ ክልል መምህራን ማህበር ተወካዮች ጋር ተወያዩ

በውይይቱ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዩሐንስ ቧያሌውና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፍአለ እንዲሁም 260 የመምህራን ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ተሳታፊዎች ለመምህራን የሚከፈለው ደመወዝ እና የሚሰጣቸው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

የመምህራን ደረጃ እድገት ዝቅተኛ መሆኑን እና የትምህርት ጥራት ችግር እንዳለም ነው የመምህራን ማህበር ተወካዮች ያነሱት፡፡ እዲሁም ከዚህ በፊት የመምህራን ማህበሩ በብአዴን ተፅዕኖ ሲደረግበት እንደነበረ ያነሱ ሲሆን አሁን ከድርጅት ነፃ ሊሆን ይገባል በማለት ጠይቀዋል፡፡

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው ባደረጉት ንግግር ከልማት ሁሉ ሰውን ማልማት ትልቁ ልማት ነው ብለዋል፡፡ መምህራን ትውልድን በመቅረፅ ለሀገር ግንባታ የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛሉ ሲባል ማጋነን አይደለም ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት፡፡ በመሆኑም ሁሉንም የተጠየቁ ጥያቄዎች የክልሉ መንግት አቅም በፈቀደ ሁኔታ በአጭር፣ መካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዶችን በማስቀመጥ መፍትሄ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡

ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነ እንዲሁም ለመምህራን ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥተን እንሰራል በማለት ርዕሰ መስተዳድሩ ለመምህራን ማህበር አመራሮች ገልፀዋል፡፡ አቶ ዩሐንስ ቧያሌው በበኩላቸው የመምህራን ማህበር እንደሌሎች የሲቪክ ማክበራት ከድርጅት ነፃ ሆኖ በአቻነት ይቀጥል ብለዋል፡፡ ለተነሱት ጥያቅዎችም የክልሉ መንግስት እና ድርጅቱ በጋራ በመሆን የሚፈቱት ይሆናል ነው ያሉት፡፡

አይሱዙ ሞተርስ በመጪው ሀምሌ ወር የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ በኢትዮጵያ ሊከፍት ነው

የጃፓኑ አይሱዙ ሞተር በመጪው ሀምሌ ወር በኢትዮጵያ የተሸከርካሪ መገጣጠሚያ ለመክፈት ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ካሳ ተክለብርሃን ከኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ታሮ ኩኒፉሳ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት አምባሳደር ካሳ የአይሱዙ ሞተርስ የተለያዩ የተሽከርካሪ አይነቶችን በተለይም የጭነትና ከባድ መኪና ተሽከርካሪዎች በስፋት በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን በመገጣጠም በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ሰፊ የገበያ ዕድል የበለጠ መጠቀም የሚቻል መሆኑን እና መንግሥትም አስፈላጊውን ድጋፍን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ታሮ ኩኒፉሳ በበኩላቸው በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እየተደረገላቸው ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን በጃፓን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊ የገበያ ዕድል በመጠቀም በቀጣይ በሌሎችም የኢንቨስትመንት ዘርፎችም ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው በረንጆቹ 2019 ሀምሌ ወር በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ያጠናቀቁ መሆኑን ገልጸዋል።

የማዕድን ፈቃድ

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ማዕድን ለሚያመርቱ፣ለሚፈልጉና ለሚያጠኑ አምስት ኩባንዮች ፈቃድ መስጠቱን የሐገሪቱ የማዕድን ሚንስቴር አስታወቀ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ማዕድን ለሚያመርቱ፣ለሚፈልጉና ለሚያጠኑ አምስት ኩባንዮች ፈቃድ መስጠቱን የሐገሪቱ የማዕድን ሚንስቴር አስታወቀ።ሚንስቴሩ ትናንት ባዘጋጀዉ ድግስ ፈቃድ የተሰጣቸዉ ኩባንያዎች ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዉያን ወይም ኢትዮጵያዉያን በሽርክና የሚያስተዳድሯቸዉ ናቸዉ።በፈቃድ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተነገረዉ ለኩባንዮቹ የሥራ ፈቃድ ለመስጠት ብዙ ዉጣ ዉረድ ነበረዉ።

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *