በቤኔሻንጉል ጉሙዝና አካባቢው ‹‹ለፀጥታ ችግር ምክንያት ናቸው›› ተብለው የተጠረጠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር የማዋሉ ተግባር እንደቀጠለ ነው፡፡

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 18/2011ዓ.ም (አብመድ) የማንዱራ ወረዳ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉጎጃም አማረ እና የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሐመድ አረጋ ትናንት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል፡፡

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ ደግሞ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታው ሽመልስ እና የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ካሳ ድረስ ትናንት በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ባሳለፍነው ዓርብ ዕለት በአካባቢው ሠላምና መረጋጋት ለማስፈን የተሠማራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችንና ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋል መጀመሩን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ባለፈው ዓርብ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል የመተከል ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንቻ አምሳያ እና የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ጊሳ ዚፋህ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡

Related stories   ሱዳን ክፉኛ ተመታ የወረረችውን መሬት ማስረከቧ ተረጋገጠ፤ ከዱላው በሁዋላ " ከኢትዮጵያ ጋር መረዳዳታን መልካም ግንኙነት እንሻለን" አለች

አብመድ በግጭቱ ወቅትና ከዚያም በኋላ ዘገባዎችን ሲሠራ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያዬት ግጭቱ በየደረጃው ባሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሚመራና መልሰው አስታራቂ ሆነው የሚቀርቡትም የግጭቱ አባባሾች የሆኑት ባለስልጣናት እንደሆኑ ሲናገሩ ነበር፡፡

ዘጋቢ፡- ወንዳጥር መኮንን

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *