ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከአገር የሸሸ ገንዘብ የማስመለሱ ስራ በወዳጅ አገሮች እርዳታ ወደ ጫፍ እየደረሰ ነው፤ በቅርቡ መንግስት መረጃ ይሰጣል

ከኢህአዴግ እቅፍ ውስጥ አድብቶ ያፈነገጠውና ሕዝባዊ አመጹን በመደገፍ ለውጡን የመራው ቡድን አመራሩን ሲረከብ ቅድሚያ ይፋ ያደረገው አገሪቱ የተዘረፈችውን ሃብት የማስመለሱ ስራ ከወዳጅ አገሮች ጋር በጥምረት እንደሚሰራ ነበር። ስራው ህግን ተከትሎና ግንኙነትን መሰረት በማድረግ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በይፋ ማስታወቃቸውም የሚታወስ ነው።

ቀደም ሲል በዋናነት በቻይና፣ በሲንጋፖር፣ በዱባይ እና በአሜሪካ ባንኮች በስውር ስም ገንዘብ መከማቸቱን ውስጥ አዋቂና ተቆርቋሪ ዜጎች በጓሮ መረጃ ሲሰጥበት እንደነበርም አይዘነጋም። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተገሪቲ የተሰኘውና ከየአገሩ በህገወጥ መንገድ ከአገር የሚወጣን ሃብት መርመሮ ሪፖርት ከኢትዮጵያ የተዘረፈውን ገንዘብ በአሃዝ ጊዜ ጠቅሶ ማስታወቁም የቅርብ ጊዜ ዜና ነው።

ተቆርቋሪዎች በጓሮ መረጃ ቢያወጡም፣ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተገሪቲ በመረጃ አስደግፎ  አገሪቱ የተዘረፈችውን ሃብት አስመልክቶ በወቅቱ የነበሩት መሪዎች መለስን ጨምሮ በደፈናው ” እጅ እንቆርጣለኝ” ከማለት ውጪ በተግባር የወሰዱት እርምጃም ሆነ እንቅስቃሴ አልነበረም።

ይህንን ሁሉ ጉዳይ የሚያውቀው የለውጡ ውጤት የሆነው አመራር ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ አኩራፊዎች ሃብታቸውን በመዝራት አገሪቱን የማተራመስ፣ እርስ በርስ የማጋጨት፣ የሴራ ፖለቲካ በማቀነባበር የፈጠሩትና እየፈጠሩት ያለው ጫና እንደ መንግስት ሊሰሩ ያሰቡትን እንዳይሰሩ እንቅፋት ሆኖባቸዋል። የቀድሞው አስተሳሰብና ርዝራዦች ስላልጸዱ አካሄዳቸውን በፈተና የተሞላ እድርጎባቸዋል። አሁንም ድረስ የማይፈነቀል ድንጋይ የለም።

የለውጡ አጋሮች ለሆኑ እጅግ ቅርብ የሆኑ በአሜሪካ የሚኖሩ የዛጎል ምንጮች እንዳሉት አገሪቱ የተዘረፈችው ገንዝብ ጉዳይ በጥብቅ እየተሰራበት ነው። በጉዳዩ የገንዘብ ተቋማትና ከፍተኛ መርማሪዎች አሉበት። ከዚህም ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከቻይና ጋር በዚሁ ጉዳይ ስምምነት ደርሰዋል። ከሌሎች አገራትም ጋር በጥምረት እየተሰራበት ነው።

Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

ጉዳይ ጥንቃቄን የሚጠይቅና ራሱ በመንግስት ደረጃ በሚስጢር የተያዘ መሆኑንን ያመለከቱት የዜናው ምንጭ፣ ዝርዝር መናገር ባይቻልም ጉዳዩ በቅርቡ ከዳር ይደርሳል። መንግስትም መግለጫ ይሰጥበታል የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ዋዜማ ራዲዮ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ  የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ከኢትዮጵያ ተዘርፎ በሌሎች ሀገራት ባንኮች የተቀመጠ ገንዘብን አስመልሳለሁ በሚል የተከተለው ስልት ውጤቱን ስኬታማ እንዳይሆን እንዳደረገው በሜይ ፩፮ ዘግቦ ነበር። ዋዜማ ጉዳዩ በሚስጢር አለመያዙ አንዱ ችግር እንደነበር ወደተለያዩ አገራት የተጓዙ ባለስልታናትም ቻይናን ጨምሮ የተሳካ ስራ ሳይሰሩ መመለሳቸውን ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ አመልክቷል።

የዛጎል መረጃ አቀባይ እንዳሉት ግን ከቻይና ጋር በአስቸኳይ ስምምነት ላይ ያልተደረሰው ለውጡ ምን ያህል የሚጸና እንደሆን ጥርጥር ስለነበር መሆኑንን፣ ይሁን እንጂ በአሁኑ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን እንደሚያውቁ ተናግረዋል። በአጠቃላይ ግን እሳቸው እስከሚያውቁት ደርስ መንግስት እንደዚህ አድርጎ በሚስጢር የያዘው ጉዳይ እንደሌለ አመልክተዋል።

በሲንጋፖ ተይዞ የተፈረደበት ዓይነት ምክንያቶችም በተደጋጋሚ ይፋ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምታቸውን የሰጡት የመረጃው ምንጭ፣ በቅርቡ መንግስት ይህንን አስመልክቶ ስራውን በማያበላሽበት መልኩ መረጃ እንደሚሰጥ እምነታቸው መሆኑንን አክለው ገልጸዋል።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

የሲንጋፖሩን ዜና ኢሳት እንዲህ አቅርቦት ነበር

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተዘረፈ ከ1ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዶላር ጋር በተያያዘ አንድ ናይጄሪያዊ ባለሀብት መታሰራቸው ተገለጸ። የሲንጋፖር ፍርድ ቤት ባለፈው ሃሙስ ባዋለው ችሎት ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ያላቸውና በሲንጋፖር የሚኖሩት ናይጄሪያዊ ባለሀብት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ እንዲሸሽ አድርገዋል በሚል ክስ የሶስት ዓመት እስር በይኖባቸዋል።

ገንዘቡን በተለያዩ የብሔራዊ ባንክ ሃላፊዎች ፍቃድ በመውሰድ ለናይጄራዊው ባለሀብት ሲያስተላለፉ ነበሩ የተባሉት ጓደኛቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚሰሩ መሆናቸው ታውቋል። ለናይጄሪያዊው ጓደኛ ናቸው በተባሉት በኚህ ግለሰብ ገንዘቡ ይተላለፍ እንደነበር ሲንጋፖር ቱዴይ የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል።

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምላሽ እንዲሰጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ሀሙስ የተሰየመው የሲንጋፖር ፍርድ ቤት ከ2008 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጀምሮ የነበረውንና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተወሰደውን ገንዘብ ጉዳይ ተመልክቶ ብይን ሰጥቷል ይላል።

ከ27 ሚሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወጪ ተደርጎ ኒዮርክ በሚገኝ ሲቲ ባንክ ውስጥ አካውን ተከፍቶ ተቀምጧል ያለው ፍርድ ቤቱ ከዚህ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት ያለውን ናይጄሪያዊ ባለሀብት በሶስት ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን መረጃው ያመለክታል።

በክሱ መዝገብ ላይ እንደተገለጸው በ2008 እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በሁለት ሳምንት ውስጥ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተጻፈና የ24 ክፍያዎች እንዲፈጸሙ የሚጠይቅ ደብዳቤ ላይ በተለያዩ ሃገራት ለሚገኙ አካላት ገንዘብ እንዲተላለፍ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ገንዘቡን ኢትዮጵያ ከሚገኝና ከመንግስት ጋር በተለያዩ ፕሮጀክቶች አብሮ እንደሚሰራ በሚገልጽ ግለሰብ አማካኝነት በማውጣት ሲንጋፖር ያሉ በትውልድ ናይጄሪያዊ በሆኑ ባለሀብት በከፈቱት የኒውዮርክ ሲቲ ባንክ አካውንት እንዲገባ መደረጉን ነው በክሱ ላይ የተገለጸው።

ናይጄሪያዊው ባለሀብት ኢትዮጵያ ካለው ወዳጃቸው የሚላክላቸውን በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር በሲንጋፖር ማስቀመጥ አደጋ አለው በሚል ኒውዮርክ ወዳለው ሲቲ ባንክ አካውንት በመክፈት ማስቀመጣቸውም ተመልክቷል። ገንዘቡ በተለያየ መጠን ከሲቲ ባንክ ደግሞ ወደ ተለያዩ ሀገራት እንዲተላለፍ መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል።

ናይጄሪያዊው ባለሀብት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፕሮጀክቶች ስም ከሚሸሸው ገንዘብ በኮሚሽን እንደሚያገኙ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል ከ27ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎ ከሀገር እንዲወጣ ፍቃድ የሰጡ ሃላፊዎች እነማን እንደሆኑ በዘገባው ላይ አልተገለጸም።

ኢሳት ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ብሔራዊ ባንክ ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የባንኩ አንድ ሃላፊ ለኢሳት እንደገለጹት ጉዳዩ በህግ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0
Read previous post:
አብይ አህመድ የአራት ቢሊየን ዛፍ ተከላ መርሃ ግብርን አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 4 ቢሊየን...

Close