የአልኮል መጠጥን በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከዛሬ ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል። የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112 በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ታትሞ መውጣቱ ይታወሳል።

በአዋጁ አንቀጽ 74 (4) መሰረት የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ነው የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ያስታወቁት።

በዚሁ መሰረት ከዛሬ ጅምሮ ማንኛውም የብሮድካስት ሚድያ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ ማስተላለፍ እንደማይችል ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አልኮል መጠጦችን የሚያስተዋውቁ ቢልቦርዶች መነሳት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112 ባሳለፍነው ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ይታወሳል።

አዋጁ የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅን ሙሉ በሙሉ ክልክል መሆኑን ደንግጓል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *