በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አነፍናፊ ውሾችን ለማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የዱር እንሰሳት ልማትና ጥበቃ ባላስልጣን፣ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕና የፌደራል ፖሊስ ናቸው ዛሬ ከሰዓት የተፈራረሙት፡፡

አነፍናፊ ውሾችን በአውሮፕላን ማረፊያው ማሰማራቱ በሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆኑት የዱር እንሰሳት በህገወጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡና የአደንዥ እጽ ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

አነፍናፊ ውሾች ከኒዘርላንድ ሚመጡ ሲሆን÷ ቁጥራቸውም አራት መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በአፍሪካ አህጉር ታንዛኒያ፣ ኬንያ ኡጋንዳና ሞዛቢክ በአውሮፕላን ማራፊያቸው አነፍናፊ ውሾችን ማሰማራታቸውም ይነገራል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አነፍናፊ ውሾችን ለመሰማራት ለባለሙያዎቹ ከ60 እስከ 90 ቀናት ያህል ስልጠናዎወችን እንደምትሰጥ ተገልጿል፡፡

ውሾቹ የተደበቁና የታሸጉ ነገሮችን በቀላሉ አነፍንፎ የማግኘት አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በሲሳይ ጌትነት -FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *