“በማፍረስ ቀዳሚ ሆን” ሲሉ ሃዘን ገብቷቸው ዜናውን ለዛጎል ይፋ ያደረጉት የዋሽንግተን ነዋሪ እንባ እየተናነቃቸው ኢሳትን ዛሬ በይፋ ለማፍረስ ቀጠሮ መያዙን ገልጸዋል። ይህንንም አስመልክቶ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅና ይህ ሊሆን የቻለውም ኢትዮጵያ ላይ ጥላውን የጣለው ” የዋልታ ረገጥ” አስተሳሰብ መሆንንም ተናግረዋል።

ወደሁዋላ በመሄድ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኔትዎርክ /ኢቲኤን በሚል ስያሜ ተቋቁሞ መፍረሱን ያወሱት የዜናው ሰው ኢሳት መቋቋሙ ይፋ ሲሆን፣ ከሰማንያ በመቶ በላይ ሲሰጥ የነበረው አስተያየት ” ደግሞ እንዳትፈርሱ” የሚል ማሳሰቢያ እንደነበር ያስታወሳሉ።

በትግሉ ወቅት ታላቅ መስዋዕትነት የከፈለው ኢሳት ከለወጡ በሁዋላ ባጋጠመው ችግር የኢሳት ቤተሰቦች ግራ መጋባታቸው የሚታወስ ነው። ችግራቸውን በውይይት ላምስወገድ ባለመቻላቸው እንዲለያዩ ስምምነት መደረሱ ታውቋል። በዚሁ መሰረት በተለይም በቅርቡ ከህመም አገግሞ ተንታኝ በመሆን ኢሳትን የተቀላቀለው ሃብታሙ አያሌው ፣ ኤርሚያስ ለገሰ፣ ከዘፈን ማስተዋወቅ ወደ ተንታኝነት የተዛወረው ተወልደ በየነ፣ በአጭር ጊዜ ከኢትዮ ቲዩብ ወደ ኢሳት የተዛወረው ምናላቸው ስማቸውና ርዕት ዓለሙ ከኢሳት እንደሚለዩ ታውቋል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ዜናውን የገለጹልን ተቆርቋሪ እንዳሉት ውሳኔው ” ማፍረስ ላይ የተካንን መሆናችንን ማሳያ ነው” ብለዋል። ችግርን በውይይት በመፍታት፣ አርቆ በመመልከት፣ የግል ጉዳይን መተው ሲቻል ይህ አለመሆኑ በግል አሳዝኗቸዋል። ይነስም ይብዛም ሰፊ የቅስቀሳ ስራ የሰራ መገናኛ ውስጥ በህብረት ሲሰሩ የነበሩ ወገኖች መስማማት አለመቻላቸው አገሪቱ በዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ የተዋጠች ለመሆኗ ማረጋገጫ መሆኑንን አመላክተዋል።

ሌሎች ራሳቸውን መልሰው በማደራጀት ጠንካራ ሚዲያ ለመገንባት ላይ ታች ሲሉ፣ ኢሳት ውስጥ እንዲህ ያለው ዜና መሰማቱ ማንን እንደሚያስደስትና ለነማን ተብሎ ይህ እንደሚደረግ ለአብዛኞች እንቆቅልሽ መሆኑንም ከናልደረቦቻቸው የሰሙትን ዋቢ አድርገው የዜናው ሰው ተናግረዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በውሳኔው መሰረት ከላይ ስማቸው የተዘረዘረው በሌላ ተቀራራቢ ስም ለብቻቸው ሆነው እንደሚቀጥሉ ታውቋል። ኢሳት አውሮፓ፣ ኢትዮጵያና አሜሪካ የሚገኘው ቦርድ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናና መሳይ መኮንን የተካከተቱበት ኢሳት በነበረበት እነደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል። ኢሳት በይፋ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ዜናውን በበጎ ያዩ ” አጋጣሚው ኢሳትን ወደ ፕሮፌሽናል መንገድ ለመውሰድና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ለመገንባት ይረዳል። ከድፍረት ተንታኝነት ተላቆ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የመማማሪያ መድረክ ለመፍጠር ያግዛል” በማለት አስተያየት ሲሰጡ መደመጥ ከጀመረ ሰነባብቷል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

 

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *