የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ይዘው አክሱም መግባታቸው ተሰማ። ዜናው አብዛኞችን እያነጋገረ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጉም አልጠፉም። የመንግስት መገናኛዎች ግን አብይ ሕዝብ እያወያዩ መሆኑንን ነው የዘገቡት።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዛሬ ማለዳ አክሱም ከተማ ሲገቡ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አቀባበል እንዳደረጉላቸው ፋና አመልክቷል። አዲስ አበባ ሲሆኑና መቀሌ ሲሆኑ ንግግራቸው የሚቀያየረው የትግራይ ሊቀመንበር በተገኙበት የተጀመረው ውይይት መቀጠሉን ነው ዜናው የገለጸው።

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

እንደ ፋና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአክሱም ሀውልትን የጎበኙ ሲሆን፥ በአክሱም ሃውልቶች ላይ የተጋረጠውን አደጋ በአካል መመልከት ችለዋል። ከጉብኝታቸው በኋላም ከአክሱም ከተማ ከተውጣጡ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ወጣቶች ጋር እየተወያዩ ይገኛል።

በውይይቱ ወቅትም ነዋሪዎቹ በአክሱም ሃውልቶች ላይ ለተጋረጠው አደጋ መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።የአክሱም ሃውልቶች የሃገር ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ቅርሶች በመሆናቸው መንግስት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባልም ነው ያሉት። ከዚህ ባለፈም በከተማዋ ያለውን ስር የሰደደ የውሃ ችግር ለመቅረፍ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግም ነው የጠየቁት።

Related stories   እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር - ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

በውይይቱ የተለያዩ ጥያቄዎች እየተነሱ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ማብራሪያና ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። የጣሊያን መንግስት በቅርቡ ለአክሱም ሃውልቶች ጥገና እና እድሳት ለማድረግ ቃል መግባቱ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝባዊ ውይይቱ በኋላ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ዙሪያ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *