ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር እንዲያውል ልዩ መመሪያ የተሰጠው ግብረሃይል በቡድን የተደራጁ ሌቦችን ከነመሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን ታወቀ። የተደራጁት ወንጀለኞች አዲስ አበባ ወስጥ በተከታታይ የሚፈጽሙት ወንጀል ሕዝቡን እና የዲፖሎማቲክ አካላትን አማሮ ነበር።

የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ በጥምረት የተካተቱበት ይህ ግብረሃይል በቁጥጥር ስር ካዋላቸው አንኳር የዘረፋ ሃይሉ መሪዎች እጅ መሳሪያና ከፍተኛ ንብረት እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን ይዟል።

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

መነሻቸውን ከአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ አካባቢዎች በማድረግ ዝርፊያ ላይ ከተሰማሩት መካከል ከፈረሰው መዋቅር ውስጥ የነበሩ እንዳሉበት ነው የዛጎል ምንጭ ያስታወቁት። ተደራጅተው ዘረፋ የሚፈጽሙትን ወንጀለኞች አሳዶ የመያዙ ጉዳይ በጥብቅ እየተሰራበትና ውጤት እንደተመዘገበት ያስታወቁት ምንጩ መንግስት በይፋ መግለጫ ስለሚሰጥ ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ማቅረብ እንደማይቻል አመልክተዋል።

ከሁለት ቀን በፊትምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ተወካዮችን  ማነጋገራቸውና የጋራ ግብረሃይል መቋቋሙን ማስታወቃቸው ይታወሳል። ከበጋራ ግብረ ሃይል በሳምንት ጊዜ ውስጥ በጥናት ላይ የተመሰረተ የወንጀል መከላከል እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ስልት ለመንደፍና በቅንጅት ወደ እርምጃ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱን መናገራቸው አይዘነጋም።

Related stories   “ፍትህ ለትግራይ! ሞት ለመከላከያ ሰራዊትና … በትግራይ ሕዝብ ስም ትህነግ የመዘዙ ምንጭ ላይሆን?

ግብረ ሃይሉ በተለይም በከተማው እየሰፋ የመጣውን የሞተር ሳይክል ቅሚያና ሌሎች በተናጠልና በቡድን የሚፈፀሙ የተደራጁ ወንጀሎችን በመቅጨት የከተማውን ነዋሪ ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነት ተሰጥቶታል። በአጭር ጊዜ ውስጥም ውጤታማ የሚያደርጉ የተለያዩ የወንጀል መከላከያ ስልቶችን በጋራ እንዲያወጣ፥ አቅጣጫ መቀመጡን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ማስታወቁ አይረሳም። ይህ በተባለ በሰዓታት ውስጥ ኦፕሬሽን መጀመሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ በቀጣይም ደንብረው ስፍራ የቀየሩትን ጭምሮ በርካታ ወረበሎች እንደሚያዙ አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *