የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ኦማር ሀሰን አልበሽር ክስ የተመሰረተባቸው በህገ ወጥ መንገድ ሀብት በማካበት እና በስልጣን ዘመናቸው ባወጁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሆኑን የሀገሪቱ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡

በመፈንቅለ መንግስት ባገኙት ስልጣን ለ30 ዓመታት መንበረ ስልጣኑን ተቆጣጥረው የቆዩት ኦማር ሀሰን አልበሽር፥ ለወራቶች በሀገሪቱ በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ከስልጣን መውረዳቸው የሚታወስ ነው፡፡

ኦማር ሀሰን ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎም የወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ይገኛል።

ምክር ቤቱ ለህዝባዊ አስተዳደር ስልጣኑን እንዲያስረክብ ከፍተኛ ግፊት እየተካሄደበት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ኤፍ ቢ

 

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

 

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *