የትዕግስት ልክ እንዳለው ነው በንግግራቸው መጨረሻ ያስታወሱት። ለውጡን ለማስፋትና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት የተሰራው ዓለምን ያስደነቀ ተግባር እንዲፋፋ ከልክ ያለፈ ትዕግስት ተደርጓል። አሁን ግን በዚህ የመቀጠል ሞራሉም፣ አቋምና ስነ ልቡና እንደማይኖር ነው ያስታወቁት። አያይዘውም ካሁን  በሁዋላ ምህረት እንደሌለ ነው አስረግጠው የተናገሩት።

ይህንን ያሉት የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ናቸው። በባህር ዳር ተሞክሮ የከሸፈውን የመፈንቅለ መንግስትና በጀነራል ሰዓረና ገዚአ አበራ ላይ ቅጥረኞች የፈጸሙትን ግድያ አስመልክቶ የክልላቸውን አቋም ያስታወቁት አቶ ሽመልስ ካሁን በሁዋላ በዚህ መልክ እናስባለን ለሚሉ ሁሉ መልዕት አስተላልፈዋል። በጓዶቻቸው መሰዋት እልህ እየተናነቃቸው መግለጫ ሲሰጡ የታዩት የኦሮሚያ መሪ፣ ለውጡን ለመቀልበስ በዚህ መልኩ የሚደረጉ ሙከራዎች ያለ አንዳች ምህረት እርምጃ ይወሰድባቸዋል። ለእንዲህ አይነቱ ተጋባር የተለመደው ከልክ ያለፈ ትዕግስት ብሎ ነገር የለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ለዴሞክራሲ ሲባል ከፍተኛ ደረጃ ትዕግስት መመረጡን ያወሱት አቶ ሽመልስ ከዚህ በሁዋላ አረመኔዎችን፣ ናዚዎችን፣ የሚታገስ ትዕግስት እንደማይኖር፣ ሊኖርም እንደማይችል ሲያሳስቡ ከአማራ ክልል ጎን ጓዶቻቸው ጎን እንደሚቆሙ፣ ከአማራ ክልል ህዝብ ጎን እንደሚሰለፉ በማረጋገጥ ነው።

“አንልፈሰፈስም” ሲሉ አጠንክረው የተናገሩት የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ “ኢትዮጵያዊነታችን ይበልጥ ይጠናከራል” ብለዋል። ለተጎጂዎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝተዋል።

በአማራ ክልል የተሞከረውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተቃውመው ግድያው ሊቀጥል እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ የተደረገው ግድያ ከባህር ዳሩ መፈንቅለ መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለው አመልክተዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ድርጊቱ ህገመንግስቱንና የፌደራል ስርዓቱን ለመናድ የተደረገ መሆኑንን ያመለከቱት ዶክተር ደብረ ጽዮን፣ ግድያው እንደሚቀጥል Image result for shimeles abdi and debretsion gሲያስጠነቅቁ መነሻቸው ምን እንደሆነ አላብራሩም። በትግሉ ወቅት ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩትና የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ጀነራል ሰዓረ ” ተደምረው” የአገር መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ እሳቸው ከሚመሩት ክልል የሆኑ ከፍተኛ ስድብና ” ከሃጂ” የሚል ዘለፋ በማህበራዊ ገጾች ሲሰነዘርባቸው እንደነበር ይታወሳል።

በዚሁ መነሻና ለውጡን ሙሉ በሙሉ አለመቀበሉን በይፋ የሚናገረው የህወሃት ሊቀመንበር መፈንቀለ መንግስቱን ለማውገዝ ግንባር መሆናቸው አብዛኞችን አነጋግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው የተከፋፈለውን ኢህአዴግ ወደ አንድ ሊያመጣ ይችላል የሚሉ የህወሃት ሊቀመንበርን መግለጫ በመልካም ሲያነሱት ትስተውሏል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

የሶማሌ፣ የቤኒሻንጉል፣ የድሬደዋ፣ የአዲስ አበባ፣ የአፋር … ክልሎች መፈንቅለ መንግስቱንና የጀነራሎችን ግድያ እንደሚቃወሙ አመልክተዋል። በጥብቅ ኮንነዋል። ኮሎኔል አለበል በርካታ የድርጊቱ ፈጻሞዎች በቁትር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። አዲስ አበባም ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ መኖራቸውን መንግስት ይፋ አድርጓል።

የዛጎል የአዲስ አበባ ምንጭ እንዳለው ተጠርጣሪዎች እንዳያመልጡ ሲባል በረራ በጊዜያዊነት መታገዱን አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ልክ የሶማሊያን ኦፕሬሽን ጅግጅጋ ተገኝተው እንደመሩት ሁሉ የባህር ዳሩን ቀውስ እዛው ሆነው አመራር በመስጠት  ከከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ጋር እንዲከሽፍ እንዳደረጉ አመልክቷል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *