“የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን  በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ የሁሉንም ሕዝብ ተሳትፎ የጠየቀ በመሆኑ ሰራዊቱም የዚህ ለውጥ ተጠቃሚ እና ደጋፊ ነው ” ማለታቸውን ተከትሎ ለውጡ እሳት የሆነባቸው ክፍሎች “ከሃጂ” በሚል ከሹመታቸው ማግስት ጀምሮ ሲያወግዟቸው ነበር። ጀነራሉ ግን ሁሉን ወደ ጎን በመተው አገራዊ ሃላፊነታቸውን በታማኝነት ሲወጡ ቆይተው ቅጥረኞች ገድለዋቸዋል። በጡረታ ላይ የሚገኙት ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራም በተመሳሳይ ተገድለዋል።

መንግስት ይፋ እንዳደረገው ውዱና ኢትዮጵያዊው ታማኙ ጀነራል በተገዛ ታጣቂያቸው በተተኮሰ ጥይት አልፈዋል። ይህ ባህር ዳር የተሞከረውን መፈንቅለ መንግስት ተስታኮ የተካሄደው የተቀነባበረ ግድያ አገሪቱን ለማተራመስ አጀንዳ ሰንቀው ብር የሚረጩት የሴራ ፖለቲካ አባቶች ተግባር እንደሆነ ጥርጥር የለውም።

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደተባለው ከለውጡ ማግስት ጀምሮ አገሪቱን ለማተራመስ በየአቅጣጫው የተከፈተውና የተሞከረው ዘመቻ አልሳካ ሲል አማራ ክልልን በማፍረስ፣ የአማራን ሕዝብ እርስ በርስ በማጫረስ፣ አገሪቱን ለማሽመድመድ፣ የመከላከያ ሰራዊትም ሙከራውን መቀልበስ እንዳይችል ለማስቻል ኤታማጆር ሹሙን በቅጥረኞች ለማስገደል እቅድ መያዙ ከማንም የተሰወረ አይደልም።

2019-06-23-2.png

በታሪክና በትውልድ ዘንድ ሲዘከሩ የሚኖሩት ሰአረ መኮንን ሲገደሉ በመከላከያ ውስጥ በሚፈጠር መራበሽ አዲስ አበባንም ለማንደድና ለማተራመስ የሚያስችል እቅድ እንደነበር መረጃዎች በሚወጡበት በአሁኑ ሰዓት፣ከፍተና በጀት ያላቸው የዲጂታል አርበኞች በማህበራዊ ገጽ የሃሰት ቅስቀሳቸውን በአማራ ስም እያሰራጩ ነው። ሙከራው ህዝብን ማተራመስ በመሆኑ ህዝብ ተጨማሪ ቀውስ እንዳይፈጠር ድርጊቱን ነቅቶ እንዲጠብቅ ከየአቅጣቻው ጥሪ እየቀረበ ነው።

መንግስት ነጻ ያወጣቸው አሳምነው ጽጌ መሩት የተባለው መፈንቅለመንግስት ቢከሽፍም የክልሉ መሪ ዶክተር አምባቸው መኮንንና ፣ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ አዘዘ ዋሴ ህይወታቸው ማለፉን መንግስት ዛሬ ማለዳ ይፋ አድርጓል። የክልሉ አቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ በጸና መቁሰላቸውም ተመልክቷል።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አሳምነው ጽጌ የመንግስት የጸጥታ ሃይል እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠይቃቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸውና ተኩስ በመምረጣቸው ህይወታቸው ተገድለዋል የሚሉ መረጃዎች ቢወጡም መንግስት መሸሻቸውን ነው ይፋ ያደረገው። የአማራ ህዝብና ለአማራ እንቆረቆራለን የሚሉ ወገኖች ይህንን አስፈሪ ጊዜ  በማስተዋል ማሳለፍ ካልቻሉ በተደገሰላቸው የዓመታት የክፉዎች ወጥመድ ውስጥ በፈቃደኛነት የመቀርቀር አደጋ ውስጥ እንደሚገቡ ከወዲሁ አገር ወዳዶች እየመከሩ ነው።

“ለአማራ ትግል” መሪ መሆኑንን የሚናገረው ሄኖክ የሺ ጥላ ” እኛ” ሲል በእነ ዶክተር አምባቸው ላይ የተፈጸመውን ግድያ የድል ውጤት አድርጎና አሞካሽቶ አቅርቦታል። እንደሚቀጥልም በመጥቀስ ለፋኖ ጥሪውን አቅርቧል።

Image may contain: text

መንግስት ማለዳ ላይ የሚከተለውን መግለጫ አሰራጭቷል። ትክክለኛ መረጃ በማከታተል ሰለሚሰጥ ህዝብ በሃሰተኛ መረጃ አከፋፋዮች እንዳይወናበድም አሳስቧል።

2019-06-23-1.png

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *