የቀድሞው የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር ችግኝ በተከሉበት የቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የመታሰቢያ ፓርክ ሊሰራላቸው ነው፡፡

በመታሰቢያ ፓርኩ ውስጥ የጀኔራሉን ክብር በሚመጥን መልኩ የማስታወሻ ሀውልት እንደሚሰራላቸው የከንቲባ ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

ችግኙን ከተከሉበት ከቦሌ ሩዋንዳ ጀምሮ እስከ አትላስ ሆቴል ያለው ጎዳናም በስማቸው እንዲሰየም የከተማ አስተዳደሩ ወስኗል፡፡

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

በከተማው የሚገኙ የስነ ህንጻና የስነ ጥበብ ትምህርት ቤት ባለሙያዎችም የጄኔራል ሰዓረን የማስታወሻ ሀውልት ንድፍ ሰርተው አጠናቀዋል፡፡ የመታሰቢያ ፓርኩን የአዲስ ከተማ አስተዳደር በባለቤትነት የሚያስገነባው ይሆናል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *