“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከጸጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ሃይል በቅርቡ በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ በተፈጸመው የግድያ ወንጅል ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ

ሰኔ 15 ቀን 2011 በባህር ዳር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ የመፍንቅለ መንግስት ለማድረግ በተፈጸመ አሰቃቂ የወንጅል ድርፈጊት ከፍተኛ የክልል እና የመከላካያ ሃላፊዎች ህይወት እንዳለፈ እንደዲሁም ሌሎች የጸጥታ አካላት እንደሞቱና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከጸጥታና ፍትህ የጋር ግብረ ሃይል መገለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ የተጠነሰሰው ሴራ በአማራ ክልል ህዝብ፣ በክልሉ እና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥረት የከሸፈ ሲሆን፥ ወንጀል ፋፃሚዎችን ለህግ ለማቅረብ የወንጀል ምርመራ ቡድን በማቋቋም የተጠናከረ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ግብረ ሃይሉ ሰኔ 20 ቀን 2011 በሰጠው መግላጫ በክልሉ 212 እና በአዲስ አበባ 43 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና በቀጠይ የሚደረስበትን ውጤት ለህበረተሰቡ በተከታታይ እንደሚያሳውቅ መግለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት ግብረ ሃይሉ ከባህር ዳር እስከ አዲስ አበባ በተዘረጋ ትስስር የተፈጸመውን ውስብስብ የወንጀል ሂደት በማጣራት ያገኛቸውን ውጤቶች ለህብረተሰቡ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶቷል፡፡

በዚህም ይህ መገለጫ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ በባህር ዳር 213 በመፍንቅለ መንግስቱ በመሳተፍ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም የክልሉ ልዩ ሃይል አመራር አባላት፣ የክልሉን የጸጥታ መዋቅር የሚመሩ ከፍተኛ ሃላፊዎች እና አባላት እንዲሁም ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች መካተታቸውን በተካሄደው ምርመራ ታውቋል፡፡

ከዚህ በፊት ከተገለጸው መግለጫ በተጨማሪ ግብር ሃይሉ ባደረገው ክትትልና ምርመራ ከተጠርጣሪዎቹ 59 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች እና በርካታ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ወንጀል ፋፃሚዎቹ የጠነሰሱትን ሴራ የሚመሩባቸው የተለያዩ የስልጠና ማንዋሎች እና የደህነነት አደረጃጃት መዋቅሮችም ተገኝተዋል፡፡

በመፈንቅለ መንግስቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተያዙ ተጠርጣሪዎች ድርጊቱን ሲመራው እና ሲያቀነባብረው ከነበረው ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እንደነበራቸው ተረጋግጧል፡፡

ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ቀደም ሲልም በህ ገወጥ መንገድ ለመንቀሳቀስ እና ራሱን ለመደበቅ በማሰብ የራሱ መኖሪያ ቤት እያለው በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 288 በአቶ ወዳጆ ማሞ ተመዝግቦ በሚታወቀው ቤት 17ኛ የቤቱ ነዋሪ በመምሰል የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የመታወቂያ ካርድ በማውጣት የተለያዩ የወንጀል ድርጊት ፈፃሚ ቡድኖችን ስያደራጅ እንደነበረ በምርመራው ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በተያያዘም በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ ኖኖ ቀበሌ የሚገኘው የብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው ጽጌ መኖሪያ ቤት ሲበርበር አንድ ክላሽ እንኮቭ፣ አንድ ራቫ ፎር ተሸክርካሪ፣ የተለያዩ ሰነዶች እና ወደፊት የሚጣራ ሆኖ የከበሩ ድንጋዮች የተቀመጡበት የባንክ ደብተር በማስረጃነት ተይዘዋል፡፡

ሃምሳ አላቃ ፈቃዱ ሃብታሙ የታባለ የቀድሞ መከላከያ አባል የነበረ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አሰልጣኝን ብርጋዴር ጀነራል  አሳምነው የቅርብ ሰው ከብርጋዴር ጀነራሉ ባለቤት ወይዘሮ ደስታ አሰፋ ጋር በተጠቀሰው መኖሪያ ቤት ተሸሽጎ መያዙን እና ሁለቱም በቁጥጥር ስር ውለው ምራመራው እየተጣራ እንደሚገኝ ግብረ ሃይሉ አስታውቋል፡፡

በዚሁ በቡራዩ ከተማ በሉ ከታ ቀበሌ በብርጋዴር ጀነራል አሳማነው የተመዘገበ ሌላ መኖሪያ ቤት እና በቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ሃያት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በስሙ ተመዝግቦ የተገኘው ባለ 3 መኝታ ቤት ኮንዶሚኒየም ውስጥም የተለያዩ ሰነዶች እና ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ተገኝቷል፡፡

በሰበታ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አንድ ማካሮቭ ሽጉጥ ከበርካታ ጥይቶች ጋር እና በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረውን የአደረጃጀት ትስስር በአስረጅነት ከሚጠቅሱ ሰነዶች ጋር በግብረ ሃይሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ እና ሌሎች በቁጥጥር ስር በዋሉት አመራሮች ተሞክሮ ከከሸፈው መንቅለ መንግስት የደህነነት እና ውትድርና ስልጠና የወሰዱ መኖራቸውም ታውቋል፡፡

ይህን ስልጠና የወሰዱ ሃይሎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ግድያ እና የተደረጃ ዘረፋ ለመፈፀም እና ለማስፈፀም ብሎም ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦችን ለማጋጨት ተልዕኮ እንደተቀበሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተለይም በአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች እና በአዲስ አበባ ከተማ ረብሻና ሁከት ለመፍጠር ህዝብን ለማሸበር እንዲሁም በተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎች ላይ የግድያ ወንጅል ለመፈፀም መሰማራታቸውም በምርመራው ተረጋግጧል፡፡

በሌላ በኩል ተጠርጣሪዎቹ ለወንጀል ድርጊታቸው ማስፈፀሚያ የሚሆን ገንዘብ ቁሳቁስ በማሰባሰብ ስራ ላይ እንደተሰማሩ ግብረሃይሉ ባደረገው የማጣራት ሂደት አረጋግጧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ግድያ ጋር እና ከባህር ዳሩ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ 60 ተጠራጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራ እና የማጣራት ስራ እየተከናዎነ ይገኛል፡፡

በተደረገው ብርቱ ክትትል ለሽብር እና ዝርፊያ ሊውሉ የተዘጋጁ ብዛት ያላቸው የጦር መሳሪዎች መሰል ጥይቶች እና 84 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተያያዘም 10 ተጠርጣሪዎች የተለያዩ ሀገራትን ገንዘብ ኖቶች በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ እና ለወንጀል ድርጊት ሊጠቀሙ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ክትትል እና ፍተሻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጸጥታና ፍትህ የጋራ ግብረ ሃይሉ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩትን ለፍርድ የማቅረብ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እያሳወቀ የተጀመረውን የህግ የበላይነት የማስከበር እንቅስቃሴ በፍጹም ለድርድር እንደማያቀርብ ያስገነዝባል፡፡

ህብረተሰቡ በተለይም የአማራ ክልለ ህዝብ እና የፀጥታ ሃይል ሰላሙን በማስጠበቅ እንዲሁም ተጠርጣሪዎችን ለህግ በማቅረብ ላበረከተው ከፍተኛ ሚና ግብረ ሃይሉ ምስጋና እያቀረበ ማኛውም ስጋት ተወግዶ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ለሚከናወነው ተግባር አሁንም ህብረተሰቡ እንደወትሮው የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል የጋራ ግብረ ሃይሉ ማሳሰብ ይወዳል፡፡

መንግስት በቀጣይነት የሃገሪቱን ብሄራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ የተሟላ ቁመና እንዳለው እየገለጸ የዜጎችን ሰላም እና ደህነነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም የሽብር እንቅስቃሴ ለአፍታም ቢሆን እንደማይታገስ ግብረ ሃይሉ በድጋሜ ያረጋግጣል፡፡

ህብረተሰቡ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ሆን ተብለው ከሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎችና አሉባልታዎች እንዲጠንቀቅ ግብረ ሃይሉ እየገለጸ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በማድረግ ከተፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች ጋር በተያያዘ ተካታታይ መረጃዎችን ለህብረተሰብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የሀገር መከላከያ፣ የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ብሄራዊ መረጃ እና ደህነነት አገልግሎት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅነት ኤጄንሲ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ የሰጡት መግለጫ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30 ፣ 2011 ዓ.ም

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል
0Shares
0