ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

“አጥፍቶ መጥፋት – የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መሪዎች መጨረሻ ነው”


በማውቅም ይሁን ባለማወቅ፣ በመገዛትም ይሁን በማሻሻጥ በዚህ በመጨረሻ ሰዓት ኢትዮጵያ ላይ ለምትፈርዱና ለምታስፈረዱ የመጪው ትውልድ ጠላቶች እባክቹህን ለብ ግዙ። ሰው ቢሞት ሰው ይተካል። ንብርተም ተለዋጭ አለው። የተሰበረም ይጠገናል። የጎበጠም ይቀናል። አገር ምትክ የላትም። በሴረኞች ወጥመድ ውስጥ የምትዋኙ ሁሉ እባካችሁን አቁሙ።


ላለፉት ሁለት ዓመታት ግድም ላይበርድ ውስጥ ውስጡን ሲግም የነበረው የኢትዮጵያ ጉዳይ አሁን ወደ መገባደጃው እየተቃረበ ያለ ይመስላል። የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሆኖ ተቋቁሞ፣ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር እየተባለ አገር መርቶ፣ ከሃያ ሰባት ዓመታት በሁዋላ ወደ ተፈጠረበት ሰፈር የገባው የነጻ አውጪ ቡድን ከኢህአዴግ ግንባርነት ሊወጣ መሆኑንን ይፋ አድርጓል። ዜናው “አጥፍቶ መጥፋት – የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መሪዎች መጨረሻ ነው” ተብሏል።

ነጻ አውጪ ግንባሩ አስቸኳይ ስብሰባ ካደረገ በሁዋላ ማምሻውን ባሰራጨው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው በአማራ ክልል ለተከሰተው ግድያ የክክሉ መሪ ፓርቲ አዴፓ ሃላፊነቱን እንዲወስድ ጠይቋል። ይህም ብቻ አይደለም ክልሉ ትምክህተኛ ሃይሎች እንዳሻቸው እንዲንቀሳቀሱ በመፍቀዱ መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል።

በአማራ ክልል ከፈተኛ ባለስልጣኖች ግድያ ጀርባ እጅ መኖሩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ካስታወቁ በሁዋላ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጦ ” አዴፓ ተጠያቂ ነው” ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ከወር በፊት ራሱን የመገንጠል ሃሳብ እያጤነ መሆኑንን መሪው ተናገረው ነበር።

” እኔ የኢትዮጵያ ጅነራል ነኝ” ሲሉ ለጎጥና ለነጻ አውጪ አስተሳሰብ ጀርባቸውን የሰጡት ኤታማዦር ሹም ሰዓረ መኮንን እንዴት ተገደሉ? ማን አስገደላቸው? ለምንስ ዓላማ ተገደሉ? ምንስ በደሉ? የሚለው ጥያቄ ከህልፈታቸው ጀምሮ አሁን ድረስ በስፋት መነጋገሪያ ነው።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

በተለይም ባልደረባቸው ብርጋዴር ጀነራል አበባው ” የፈለገ ይምጣ አፈርጠዋለሁ”  ሲሉ በአስከሬን ሽኝት ወቅት የጀነራሉን ውድ የኢትዮጵያ ልጅነት ሲናገሩ  ህይወታቸውን አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበር ነው ይፋ ያደረጉት።

መደመራቸውና ለውጡን ለማስቀጠል በመወሰን ኢትዮጵያዊነታቸውን በገሃድ እየመሰከሩ መከላከያውን መምራት የጀመሩትን ሰዓረ በተደጋጋሚ “ከሃዲ” በመባል ፕሮፓጋንዳ ሲነዛባቸውና በትልልቆቹ የህወሓት ባለሥልጣናት ሳይቀር የትግራይ ጠላት ተደርገው ሲፈረጁ ቆይተዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የትግራይ ተቆርቋሪ ነን በሚሉ የሰዓረ መኮንን ፎቶ በየቦታው ተዘቅዝቆ ሲሰቀልና ሲረገጥ ነበር።

የአባቱ አስከሬን ፊት ቆሞ መናገር የተሳነው ልጃቸው ትንፋሹን ውጦ፣ ሲቃውን ገድሎ ሳግ እየተናነቀው ያለው ነገር ቢኖር ” አባቴ ኢትዮጵያዊ ነው” የምትለዋን ቁልፍ ጉዳይ ነበር። ” ኢትዮጵያ ትቀጥላለች” ሲል ሳጉ ጉሮሮውን እያረደው የተናገረውና ከዚያ በላይ ምንም ሊል ያልቻለው የሰዓረ ልጅ መልዕክት ግልጽና ግልጽ መሆኑንን በርካቶች በገሃድ አውርተውታል።

በድሮው አውሮፕላን ማረፊያ የደህንነት ቢሮ የቀጣይ ኢላማ አራማጆች ላይ እርምጃ ከተወሰደ በሁዋላ ቀጣዩ የባለስልጣናት ግድያና የተቋሞች ወረራ መክሸፉ ጉዳይን አቀለለው እንጂ ሴራው የተጎነጎነው በሰፊው እንደነበር ሚስጥር አዋቂዎች አሁንም የሚያጉተመትሙትና ጊዜ የሚጠብቅ ጉዳይ ነው።

ከሳምንታት በሁዋላ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ራሱ ጠፍጥፎ ሲጋልበው ከነበረው ግንባር እንደሚወጣ በማስጠንቀቅ ግድያዎቹ በገለልተኛ ወገኖች እንዲጣሩ ሲጠይቅ፣ የንጹሃን ድምና መከራ የሚጮህበትን ጌታቸው አሰፋን አስመልክቶ ያለው ነገር እንደሌለ የትግርኛ መግለጫውን ያነበቡ አስታውቀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ካብቢኔ ለይቶ የአሜሪካ ተላላኪ በማድርግ የሚዘልፈው የነጻ አውጪው አመራር ከግንባሩ ለመውጣት ያስፈራራውና የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ባስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን የጠየቀው የምስራቅ አፍሪቃ ሰላም አደጋ ላይ ወድቋል በሚል ተመልሶ ወደ ስልታን የሚመጣበትን የፖለቲካ ገበያ ለመጫወት እንደሆነ አፍታም ሳይቆይ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

ሃያ ሰባት ዓመታት በነፍጥና ነፍጥን ያነገቡ የነሳ አውጪ ሃይሎቹን በማሰማራት፣ ደህንነቱንና የፌደራል ፖሊስ ሃይሉን ብቻውን በመቆጣጠር ኢትዮጵያን ሲጋልባት የነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ለሲዳማ ጥያቄ ሲሰጥ የነበረው ምላሽ ጥይትና እስር እንደሆነ ያስታወሱ ” አገሪቱን ለማተራመስ በሚጠቅመው አጀንዳና በተካነበት ሴራ ለሚያመርተው ክፋት ከፍተኛ በጀት የሚመድበው ህወሃት ዛሬ ይህንን የሚለው አገሪቱን ውጥረት እንዲያውካት ካለው ልዩ ፍላጎት የተነሳ እንጂ ለሃዋሳ ህዝብ አዝኖ አይደለም። ቢሆንማ ዛሬ ተስፋ የተገባለትን ጥያቄ አንስታችኋል በሚል ንጹሃንን ባልገደለ፣ ባላሳደደና ቶርቸር ባላደረገ ነበር” ሲሉ መግለጫው እንደተሰማ የአካባቢው ነዋሪዎች አስተያእታቸውን ሰንዘረዋል።

የቅማንትን አርሶ አደሮች በማደራጀት፣ በማሰልጠንና እጅግ ዘምናዊ መሳሪያ በማስታጠቅ፣ የአማራ ክልልን ለማተራመስ የሚሰራው ይሕው የነጻ አውጪ ሃይል እንደሆነ የአማራ ክልል አመራሮች በስፋት ሲናገሩ እንደነበር የሚታወስ ነው። በቅማንት ብቻ ሳይሆን ለውጡ ባልተቀበሉ አመራሮችና ካድሪዎች መካከል በመስረግ ክልሉን ለማመስ በቤኒሻንጉል በኩል በውክልና ሲንቀሳቀስ እንደነበር የሚከሰሰው ህወሃት በተካነበት የሴራ ፖለቲካ የአማራ ክልል ህዝብ ሃዘን ላይ እንዲወድቅ ማድረጉን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂዎች፣ ህወሃት አዴፓ ላይ ሁሉን ጉዳይ መዘፍዘፉ የእሽቅድድም ጉዳይ ነው ብለዋል።

ክልሉ ለህወሃት ውንጀላ መልስ እንደሚሰጥ የጠቆሙት ክፍሎች ህወሃት በደለኛ፣ ክፉ ሕዝብ አድርጎ ዝመቻ ሲከፍተበት የኖረውን የአማራ ሕዝብ አንገት አስደፍቶ ሲያበቃ ያወታው መግለጫ ምን አልባትም የክልሉን ሕዝብ እንደ አንድ ሊያቆም የሚችል አጋጣሚ እንደሚሆን መረጃዎች እየወጡ ነው።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ በተፈጠረበት ክልል ሕዝብን ምሽግ አድርጎ የተቀመጠው የዚህ ነሳ አውጪ ግንባር አንጋፋ አመራር ከዳር ሆኖ በሚያዘው መሰረት ህወሃት ከግንባሩ ለመውጣት ማስፈራራቱ ብቻ ሳይሆን ተመልሶ ወደ ስልጣን የመምጣት ዝንባሌውን ማሳየቱ ተመልክቷል።

“አጥፍቶ መጥፋት – የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መሪዎች መጨረሻ ነው” ሲሉ ሃሳባቸውን የሰጡ የቀድሞ የድርጅቱ አባል ሕዝብን የሚያሳዝኑና ሕዝብን በጅምላ የሚፈርጁ አስተያየቶችን ከመስጠት መቆጠብ አግትባብ መሆኑንን አስገንዝበዋል። ከኢትዮጵያ መለየትም ሆነ   ከኢትዮጵያዊ ወንድሞች ጋር ጦር መማዘዝ ለትግራይ ሕዝብ የሚፈይደው አንዳችም ጉዳይ ባለመኖሩ ጉዳዩ ያገባናል የሚሉ ወገኖች በሙሉ በጥሞና እንዲያዩትም መክረዋል።

ዶክተር አረጋዊ በርሄ በቅርቡ ” የትግራይ ሕዝብ ታግቷል” ማለታቸውን በማስታወስ ” ህወሃት ለሰው ነበስ ተቆርቁሮ ለመከራከር፣ ከዛም አልፎ የሰው ህይወት የልዩነቱ መነሻ ሆኖለት እርምጃ እስከመውሰድ መድረሱ አሰገራሚ ነው። ከቻለ ካሃውዜን እልቂት ጀመሮ በየጊዜው ላጠፋቸው ነጹሃን አስቀድሞ ይቅርታ ይጠይቅ፣ እጁ ላይ የሚጮኸውን ደም ይጠብ፣ ሃጢያቱን ይናዘዝ። ከዚያ በሁዋላ እናምነዋለን” ሲሉ አስተያየታቸውን ድምድመዋል። በቅርቡም ሰፊ መብራሪያ እንደሚያቀርቡና እንደሚያሰራጩ ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ላነሳው ክስ ይህ እስከታተመ ድረስ የሰጠው ምልሻ የለም። ይሁን እንጂ ከግድያው ጀርባ የህወሃት እጅ እንዳለበት መረጃ መገኘቱን ግን አንዳንድ ሃላፊዎች በገደምዳሜ እየገለጹ ነው። በዚህ ውንጀላ ዙሪያና በማስፈራሪያው ዙሪያ የሌሎች አቻ ድርጅቶች አቋምም ለጊዜው ይፋ አልሆነም።

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0
Read previous post:
U.S. and Ethiopia to conduct Justified Accord (JA) 2019

Approximately 1,100 military and government personnel will participate in the annual, combined, joint military exercise...

Close