መንግስት ለሃዋሳና አካባቢያዋ ቀውስና ሰብአዊ ጥፋት ተጠያቂ ያላቸውን እየለቀመ መሆኑና አሁን ላይ ሃዋሳ ሰላም መስፈኑንን ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው። መተነኛ ስጋት ቢኖራቸውም የሽማግሌና የምሁራን ምክር እንዲሁም አምስት ወር መተበቅ አቅቷቸው አገር ሲያተራምሱ የነበሩት መያዛቸው አካባቢው ፋታ እንዲያገኝ አድርጎታል ብለዋል።

አንድ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ እንደሚናገሩት ከሆነ  የተወሰኑ የሲዳማ ወጣቶች ነን ባዬች ለዝርፊያና ንብረት ለማቃጥል ሲነሱ ፖሊስ እያየ ከማስጣልና ከመከልከል ይልቅ ከለላ ይሰጥ ነበር። መንገድ የሚዘጉ ወጣቶችን እንዲሸሹ በማድረግ ተባባሪነቱን ያሳይ ነበር። በመሆኑም የመከላከያ ሰራዊትና ልዩ የፖሊስ ሃይል ተቀናጅተው እርምጃ መውሰዳቸው አግባብ ነው። በአፋጣኝ ሰላም እንዲመለስ አድርጓል።

“ነገ ክልል መሆናችንን እናውጃለን” በሚል ለቢቢሲና ለተለያዩ ሚዲያዎች መግለጫ የሰጡት የኢጄታ መሪዎች መንግስት ባስቀመጠው የአፈጻጸም ሂደትና ምርቻ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት ባስቀመጠው አግባብ ከቶውንም እንደማይስማሙና በራሳቸው ሃይል የክልነት አዋጅ እንደሚያሳውጁ ተናግረው ነበር።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ለምንግስት ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት መንግስት ሌሎችን በሚያስተምር መልኩ እርምጃ ይወስዳል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፓርላማ ላይ ቀርበው ጥያቄው በህጋዊ መንገድ እየሄደ ነው መታፈስ አስፈላጊ ነው። ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ ከወትሮው በተለየ አክርረው መናገራቸውና ማስተንቀቃቸው የዚሁ የከረረ እርምጃ መገለጫ እንደሆነ ገልጸዋል።

ቢቢሲ የሚከተለውን ዘግቧል። ዛሬ ረፋድ ላይ በሐዋሳ ከተማ አለመረጋጋቶች ቢኖሩም አሁን አንፃራዊ መረጋጋት እንዳለ የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ተጠባባቂ ቢሮ ሃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በሁሉም ከተማይቱ አካባቢ የተፈጥረውን ግጭትና ሁከት ለመቆጣጠር እንደተቻለ ገልፀው ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጠናከሩንም ጨምረው ተናግረዋል።

ግጭቱ የተነሳው ሐምሌ 11፣2011 ዓ.ም የሲዳማ ክልልነት መታወጅና በዞኑ ምክር ቤት ተወስኖ ይፋ መሆን አለበት በማለት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰንደቅ አላማና ታፔላዎችን መትከል አለብን በሚል ኃሳብ የተነሱ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመጋጨታቸው እንደሆነ ኃላፊው ይናገራሉ።

በርከት ያሉ ከከተማም ሆነ ከገጠር የመጡ ወጣቶች ወደ ባህላዊ ስፍራ መሰብሰቢያና ሌሎች አካባቢዎች በጥዋት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርና በኋላም ስብስቡ እንደጨመረ ይናገራሉ።

በተለይም በተለምዶ አቶቴ፣ ዲያስፖራ፣ አዲሱ ገበያና ዶሮ እርባታና በሚባሉ አካባቢዎች ላይ ሰፋ ያለ ግጭት ነበር ይላሉ። የፌደራል ፖሊስ፣ መከላከያ፣ የክልሉ ኃይልና እንዲሁም መደበኛ ፖሊስ በጋራ በመቀናጀት እነዚህ አካባቢዎች ላይ እንደተረባረበ ገልፀው በተለይም የመንገድ መዝጋት ስራዎች በስፋት እንዳይቀጥሉ እንደተሰራም ኃላፊው አስረድተዋል።

የሲዳማ ክልልነትን ሲያውጁImage copyrightREUTERS

በዚህም ውስጥ ለውስጥ ባሉ መንገዶች ላይ ጎማ የማቃጠል መንገድ የመዝጋት ስራዎችም ቢኖሩም አሁን መንገዱን የመክፈት ስራም እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል።

አንዳንድ የአይን እማኞች የተኩስ ልውውጥ ነበረ ቢሉም ኃላፊው በበኩላቸው “ከተኩስ በመለስ በትዕግስት ሰራዊቱ ይሄንን ግርግርና ግጭት ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ ነው እስካሁን የቆየው፤ በዚህ ቦታ ላይ የተፈጠረ ተኩስ አለ የሚል ሪፖርት የለንም። ” ብለዋል።

ዝርዝሩ በቀጣይ ቀናት የሚታወቅ ይሆናል በማለት “በተጨባጭ ግን በአብዛኛው ሊባል በሚችል ሁኔታ ወደ ከፋ እርምጃ ሳይሄዱ የተሰበሰቡና ግርግር የሚፈጥሩ ኃይሎችን ለመበተን ጥንቃቄ በተሞላ ሁኔታ ተሰርቷል” ብለዋል።

የተገደለ ሰው እንዲሁም በአካባቢው የቆሰሉ ሰዎች አሉ ቢባልም ኃላፊው እስካሁን ባለው ምርመራ የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ገልፀው ነገር ግን “በርካታ ግጭቶች ስለነበሩ መቁሰል ሊኖር ይችላል” ብለዋል። ዝርዝሩ በቀጣይ ምርምር እንደሚገለፅ ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *