ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

በዲሲ በተደረገ የድጋፍና የተቃውሞ ሰልፍ – የመፈክር ድብድብ

ለውጡን የሚመሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በማውገዝና በመደገፍ በተመሳሳይ ቦታ፣ በተመሳሳይ ቀን በተካሄደ ሰልፍ የመፈክር ድብድብ ተካሄደ። በስፍራው ተገኝተን እንደታዘብነው በጅምላ የሚታሰሩ ወገኖች እንዲፈቱ ሲጠየቅ እስክንድር ነጋና ተመስገን ደሳለኝን ተወድሰዋል። በተቃራኒው እስክንድን ነጋና ተመስገን ደሳለኝ በጋዜጠኛነት ካባ ወንጀል እንደሚፈጸሙ ተስተጋብቷል። ተመስገን ደሳለኝ የአገር መከላከያ ሚስጢር ይፋ በማድረጉ ለፍርድ እንዲቀርብ ተጠይቋል።

እንደተለመደው ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተሳታፊዎች ከሁለቱም ወገኖች ባይሳተፉም በሰልፉ ላይ ከሁለቱም ወገኖች የተሰሙት መፈክሮች አንደኛው ወገን ሌላኛውን ወገን የሚቃረንበት ነበር።

የ360 የዩቲዩብ ተንታኝ ኤርሚያስ ለገሰ የአዲስ አበባ ባለ አደራ / ባልደራስ ምክትል ሰብሳቢ እንጠራው በተነገረለት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተቀላቅለው የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙት ወገኖች ተገኝተዋል።

Related stories   አውሮፓ ህብረት - ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ

ከመፈክሮቹና የሰልፉ መሪ አቶ ኤርሚያስ ከተናገሩት ንግግር በቂ መረጃ በመገኘቱ ከሰልፉ ተሳታፊዎች ተጨማሪ መረጃ ማሰባሰብ ያላስፈለገው የዛጎል ዘጋቢ እንዳለው፣ ከሁለቱም ጎራ በሰልፉ የታደሙ እርስ በርስ ያደረጉት መጎነታተል እጅግ የሚወገዝ ነው። ሃሳብን በነጻ መግለጽ ማንም አካል ማንንም ሊከለክል ስለማይችል ለወደፊቱ መከባበርና የሃሳብን ልዩነት ከስሜት በጸዳ አግባብ መግለጽ እንደሚገባም አመልክቷል።

በሰልፉ ላይ ሲሰሙ ከነበሩት መፈክሮች መካከል

” እኔ እስክንድር ነኝ፤ እኔ ተመስገን ነኝ፤ አገሪቱን እየመራ ያለው መንግስት በእነ እስክንድር ላይ የሚያደርገውን ማሳደድና ማሳቀቅ ሊያቆም ይገባል፤ አዲስ አበባ የሁሉም ብሄር ብሄረ ሰቦች ከተማ ናት፤ ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም…” የሚሉትን መፈክሮች ሰልፉን ያዘጋጁት ወገኖች ደጋፊ የሆኑት ሲያሰሙ

Related stories   አየር ሃይል " ትዕግስትም ልክ አለው" ሲል ለሱዳን ምክረ ሃሳብ ሰጠ

” እስክንድር ነጋ ወንጀለኛ ነው፤ በጋዜጠኛነት ካባ ጥላቻን ይሰብካል፤ ተመስገን ደሳለኝ ወንጀለኛ ነው፣ የአገር ሚስጢር የሚያባክኑ ለፍርድ ይቅረቡ፤ አዲስ አበባ የሁሉም ናት፤ ” የሚሉት መፈክሮች በሌሎች ወገኖች ከተደመጡት መካከል ናቸው።

” በአማራ ክልል ያለው የጅምላ እስር ሊቆም ይገባል፤ አማራነት ከኢትዮጵያዊነት ጋር አይጋጭም፤ አዲስ አበባ የሁሉም ናት ብሎ አማራ ያምናል፤ ፍትህ ያለ ጥፋታቸው ለታሰሩ የአማራ ክልል ጀነራሎች፤ ” ሲሉ የተቅውሞ ሰልፉን የሚደግፉ እየተቀባበሉ መፈክር አቅርበዋል።

በተቃራኒው ደግሞ ” እኩልነት የሰፈናባት ኢትዮጵያን እንፈልጋለን፣ እኩልነት የሰፈነባት አገር እንፈልጋለን፤ አንድነት ሃይል ነው፤ አሳምነው ጽጌ ገዳይ ነው፤ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ … ” በማለት የተቃውሞ ሰልፉን ተቃውመዋል።

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

ገለልተኛ ወገኖች ከሰልፉ ትዕይንት በሁዋላ ” የአማራን ስም በማንሳት ሲሰነዘሩ የነበሩ አንዳንድ መፈክሮች አስደሳች አይደሉም። በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ ያለ አገባብ የታሰሩ እንዲፈቱ መጠየቅ አግባብ ሆኖ ሳለ በሁሉም ጉዳይ ላይ የአማራውን ስም እያነሱ መፈክር ማሰማት የአማራን ህዝብ ወዳጅ አያፈራለትም። ተቀናቅኝ እንዲበዛለት የሚያደርግ ሲሆን፣ በተለይም አማራን ለማጥፋት ሌት ተቀን ለሚተጉት አመቺ ሁኔታ መፍጠር ነው” ሲሉ የተቃውሞ ሰልፍ የሚያዘጋጁ አካላት በተለይ አማራውን የሚመለከት ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ሰልፍ ካልሆነ በቀር ሁሉንም ጉዳይ ወደ አማራው ማጠጋጋት እንደማይገባ መክረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያና ሚዛን ያለው አስተያየት መስጠት ለምትፈልጉ ዛጎል የተለየ አክብሮት አላት።