‹‹ውይይቱን ያዘጋጀው የሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቅድመ ዝግጅት አላደረገም›› በሚል  ከተወያዮች በተነሳ ሐሳብ የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ ላይ ለመወያዬት የተጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተበተነ። ኮሚቴው ረቂቅ ህጉ በምክር ቤቱ ድረ ገጽ ላይ መለጠፉን ከግንዛቤ አስገብቶ ስብሰባውን መጥራቱ አመልክቷል።

ተወያዮቹ ‹‹ረቂቅ ሕጉ በእጃችን አልገባም፤ ሪፖርትም ባለመደረጉ በረቂቅ ሕጉ ላይ ግንዛቤ የሌለን በመሆኑ አንብበን እንድንወያይ ጊዜ ይሰጠን›› በሚል ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ውይይቱ የተበተነው።

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ስብሰባውን የጠራሁት ከሦስት ቀናት በፊት ሲሆን ረቂቁ በምክር ቤቱ ድረ ገፅ ላይ መለጠፉን አስታውሶ ይንኑ ከግንዛቤ በማስገባት አባላቱ አንብበውታል በሚል እመነት ስብሰባውን መጥራቱን አስታውቋል፡፡

የሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተወካይ ወይዘሮ የሺመቤት ነጋሽ ውይይቱ ለቀጣይ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ሕግ ‹‹የፀጥታ ኃይሎች በምርጫ ውድድር ጊዜ በመፃፍ እና በመናገር መደገፍ አይችሉም›› ይል እና በተከታዩ ንዑስ ረቂቅ አንቀፅ ላይ ‹‹የፀጥታ አካላቱ መለዮዋቸውን ለብሰው በፖለቲካ ድርጅት ስብሰባ ወይም በምርጫ እንቅስቃሴ መሳተፍ አይችሉም›› ይላል፡፡
ረቂቁ በምርጫ መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በእጩነት ከተመዘገቡበት ጊዜ አንስቶ የምርጫ ሂደት እስከሚጠናቀቅ በጊዚያዊነት ከሥራ ገበታቸው መልቀቅ እንደሚኖርበት የሚደነገግ ሐሳብም ይዟል፡፡

ዜናው ከአማራ ሚዲያ ተውስዶ መለስተኛ ማስተካከያ ተደርጎበታል

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *