የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በዛሬው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ2011ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ የነበረውን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች አባለት ምርጫ እና የአካባቢ ምርጫ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማካሄድ ባለመቻሉ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ በመቀበል ነው ዛሬ ያጸደቀው።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ሐምሌ 4 ቀን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጻፈው ድብዳቤ የሁለቱን ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት ምርጫን በተቀመጠው ጊዜ ማለትም ዘንድሮም ‹‹ማካሄድ አይቻልም›› ብሏል።

በቀረው አጭር የዓመቱ ጊዜ ምርጫ አስፈፃሚዎችን ለመመልመል፣ ለማደራጀት እና ስልጠና ለመስጠት በቂ ጊዜ አለመኖሩን ቦርዱ በምክንያትነት አቅርቧል።

በዚህ የውሳኔ ሐሳብ መሠረትም አሁን በሥራ ላይ ያሉት የአዲስ አበባ እና ድራዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች በሥራቸው ይቀጥላሉ።

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ በ2010ዓ.ም መካሄድ የነበረባቸው ቢሆንም በወቅቱ በሀገሪቱ የነበረው ሁኔታ ለምርጫ ምቹ ባለመሆኑ 2011ዓ.ም ላይ እንዲካሄድ ይኸው ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ኤፍ ቢ ሲ በዘገባው አመላክቷል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባንክ ሥራ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጅን እየተመለከተ ነው።

በተመሳሳይ የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጉምሩክ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ በመርመር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን እና ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ነው ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው

አብመድ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *