ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክትር) ከዚ በኋላ የሚፈጠሩ ሥራዎችን በስም ሳይቀር በመዘርዘር ለምክር ቤቱ ተጨባጭ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ተናገሩ፡፡ ሥራ ዕድል ፈጠራውም 3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ከውጭ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ለዚሁ ሥራም በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2012 ዓ.ም 3 ሚሊዮን የሥራ ዕድል የሚፈጥር የሠራተኛ እና ኢንቨስትመንት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

ኮሚቴው ተጨባጭ የሆኑ ሥራዎችን በመፍጠር የሀገሪቱን ችግሮች እንደሚያቃልል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡ ከ10 ሚኒስትሮች ፣ ከ9 ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ከሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች ከንቲባዎች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢንቨስትመንቱ ፈተና የሆነውን ሙስና፣ ቢሮክራሲ እና የኢንቨስተሮች አጋዥ ማጣት መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ በዚህ ወቅት 11 ሚሊዮን ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሚገኙ ሲሆን በየዓመቱ ከ2 እስከ 3 ሚሊዮን የሥራ ፈላጊው ቁጥር እንደሚጨምር ተጠቁሟል፡፡

በ2012 ዓ.ም ብቻ ሊፈጠር ከታሰበው 3 ሚሊዮን ሥራ ውስጥ 1 ነጥብ 4 በጊዜያዊነት እና 1 ነጥብ 6 ደግሞ በቋሚነት መሆኑ ተገልጧል፡፡
የሥራ ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት ኮሚቴው 3 ዓይነት ንዑሳን ኮሚቴዎች ያሉት ሲሆን በእነዚህ ውስጥ ሁሉም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የከተማ አስተዳደሮች ይካተታሉ፡፡

ዋናውን ኮሚቴ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ይመሩታል፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የዚሁ አካል እንደሆኑ ታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከዚ በኋላ የሚፈጠሩ ሥራዎችን በስም ሳይቀር በመዘርዘር ለምክር ቤቱ ሪፖርት እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል፡፡ ለሥራ ፈጠራ የሚውል 3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ከውጭ መገኘቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2012 በጀት ዓመት ዕድገት የሚለካው ሰውን ሥራ በማስያዝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አሁን ሊፈጠር ከታሰበው የሥራ ዕድል ውስጥ 716 ሺህ በአማራ ክልል እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

ዘጋቢ፡-አንዷለም መናን -ከአዲስ አበባ    ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 01/2011 ዓ.ም (አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *