የአውሮፓ ኅብረት በድርቅ ጉዳት ደርሶባቸዋል ላላቸው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከባለፈው የአውሮፓውን ዓመት ጀምሮ 366 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ መመደቡ ይታወቃል፡፡ የጉዳቱ መጠን አሳሳቢ በመሆኑም ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ዩሮ መመደቡ ተነግሯል፡፡ ድርቁ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳን መጉዳቱም ተጠቁሟል፡፡

የኅብረቱ ተጨማሪ ገንዘብ ለሶማሌ 25 ሚሊዮን ዩሮ፣ ለኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን ዩሮ፣ ለኬንያ 3 ሚሊዮን ዩሮ እና ቀሪውን 2 ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ ለኡጋንዳ ድርቁን መቋቋሚያ እንደሚውል ታውቋል፡፡ የኅብረቱ ሰብዓዊ ዕርዳታና የአደጋ አመራር ኮሚሽነር ክሪስቶስ ስትይሌኒድስ በቀጠናው በነበራቸው ተደጋጋሚ ጉብኝት የድርቁን አስከፊነትና ሰብዓዊ ቀውሱን መታዘባቸው እና ድጋፉ ይህንን ችግር ለመቋቋም ያስችላል ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2016 እስከ 2017 በቀጠናው ተከስቶ የነበረውን የከፋ ድርቅ ተከትሎ የምግብ ዋጋ ንሯል፡፡  አሁን እየተስተዋለ ባለው የድርቅ ሁኔታ በቀንዱ ሀገራት ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት የምግብ እጥረት ይገጥማቸዋል፡፡ የምግብ፣ የሕክምና፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ኅብረቱ ይሰጣቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ተጨማሪ ሰብዓዊ አገልግሎቶች መካከል ይገኙበታል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን – ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 01/2011 ዓ.ም (አብመድ)

ዘጋቢ፡- ኃይሉ ማሞ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *