ለውጡን በለጋ እድሜው ለማጨናገፍ በጀትና  ስልት ነድፈው የሚንቀሳቀሱ የሴራ ፖለቲካ መሃንዲሶች ሁሉም አልሳካ ሲላቸው በሃይማኖት ስም እንደሚዘምቱ አስቀድሞ መረጃ መሰጠቱ፣ በሙስሊሙ አመራርና ምዕመን መካከል የተዘረጋው ግንኙነት ጤነኛ መሆን የታሰበው መተራመስ ተግባራዊ እንዳይሆን ማድረጉ ተገለጸ።

በለቡ ከመንግስት እውቅና ውጪ እንዲፈርስ የተደረገውን መስጊድ ተከትሎ  የቀድሞው የሙስሊም እንቅስቃሴ መሪዎች መካከል ለዛጎል በሰጡት አስተያየት ” ማንም የማይሰብረው ሰላማዊ መናበብ ስላለን ረብሻው እንዳይከሰት አድርገናል። ወደፊትም እንዲህ ያለው ሴራ የሚሳካበት እድል የለም” ብሏል።

የምስጊዱ መፍረሰ እንደተሰማ በማህበራዊ ሚዲያዎች አስተያየት ሲሰጡ የነበሩ ወገኖች ” መንግስት ይህንን ድርጊት አይወቀውም” በሚል የድርጊቱን ክፋትና ልዩ ዓላማ ሲያጋልጡ ነበር። ፋና የሚለተለውን ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለቡ ቫርኔሮ አካባቢ ሰሞኑን በፈረሰው አሊፍ መስጅድ በመገኘት የሀይማኖት አባቶችን አነጋገሩ፡፡

Related stories   በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሃሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ፣ የተጭበረበረ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጭ የፈረሰውን የአሊፍ መስጅድን ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ጉብኝታቸውም ጥቂቶች በተንኮል ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ሊያጋጩ እና በሴራ ሊበትኑ ቢያስቡም እኛ ግን ችግሮችን በተሻለ መንገድ እናልፋቸዋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአምልኮ ስፍራዎችን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሁሉም የእምነት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

መስጅዱን በማፍረስ የተሳተፉ አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጎን ለጎንም መስጅዱን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባትም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ 4 ሺህ ካሬ ሜትር ተለዋጭ ቦታም ለአዲስ አበባ መጅሊስ መተላለፉም ነው የተገለጸው፡፡

ከተጀመረው የለውጥ ጉዞ የሚያስተጓጉሉንን ለመግታት አሁንም የጋራ ጥረታችን ሊቀጥል ይገባል ሲሉም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *