በተማሪዎችና በወላጆቻቸው ላይ እየተፈጠረ ላለው የስነ ልቦና ቀውስ ማን ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ለተጠየቁት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓርዓያ ገብረእግዚአብሔር “በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለሁም” ማለታቸው ተሰማ። ኮሚቴ መቋቋሙን ግን ተናግረዋል።

“በፈተናዎቹ ለተከሰተው ችግር ማን ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ለመናገር ፈቃደኛ አይደለሁም” ያሉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓርዓያ ገብረእግዚአብሔር ኤጀንሲው የተስተካለውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ውጤት ከዛሬ ጀምሮ መመልከት እንደሚቻል አመልክልተዋል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ተማሪዎች ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ውጤትን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ አስታወቀ።

ኤጀንሲው ከፈተናው የመልስ ቁልፍ ጋር ተያይዞ የነበረው እርማት ተጠናቆ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በድረ ገጹ እና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መመልከት ይችላሉ ብሏል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓርዓያ ገብረእግዚአብሔር ለኤፍቢሲ እንዳሳወቁት የፈተናው ኮድ 21 እና 22 ችግር እንደነበረባቸው ጠቅሰዋል።

ዳይሬክተሩ ቀደም ሲል በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እና በድረ ገጽ መለቀቁን ጠቅሰው የተለቀቀው ውጤት ያልተስተካከለው እንደነበር ገልጸዋል።

ከፈተናው ጋር ተያይዞ ለኤጀንሲው 10 ሺህ ቅሬታዎች መቅረባቸውን ያነሱት ዳይሬክተሩ አሁን ላይም ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ እስካሁን በሌሎች የትምህርት በአይነቶች ችግሮች ያለመገኘታቸውን አስረድተዋል።

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በፈተናዎች ላይ ለምን ተደጋጋሚ ችግሮች እንደሚከሰቱ፣ በተማሪዎችና በወላጆቻቸው ላይ እየተፈጠረ ላለው የስነ ልቦና ቀውስ ማን ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ጠይቆ ነበር። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓርዓያ ገብረእግዚአብሔር ግን “በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለሁም” ነው ያሉት።

አማራ ማስ ሚዲያ 

በሌላ በኩል ኤጀንሲው በድረገጹ ይህንን ብሏል

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ለተከበራችሁ የ2011 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች
የ2011 የፈተና ውጤት መለቀቅን ተከትሎ ከውጤቱ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ማቅረባችሁ ይታወሳል። በዚሁ መሠረት ኤጄንሲው ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሠጥቶ ባደረገው ማጣራት የስኮላስቲክስ አፕቲቲዩድ ትምህርት ኮድ 21 እና 22 የመልስ መፍቻ “Answer Key” ለማረሚያ ማሽን ሲሠጥ መቀያየር እንደነበረ ማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ መሠረት በትክክለኛው የመልስ መፍቻ መሠረት ታርሞ የተስተካከለው ውጤት ለተማሪዎች ተለቋል። በአዲሱ ውጤት መሠረት በኮድ 21 እና 22 ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል የ148,734 ተማሪዎች ውጤት በማዳግ ለውጥ አሳይቶዋል። ስለሆነም ተማሪዎች ውጤቱን በተለመደው መንገድ ኦንላይን ገብተው ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን። (ውጤታችሁን በSMS የምታዩ ተማሪዎች አዲሱ ውጤት በነገው ቀን የሚጫን ይሆናል)

በሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች በተመለከት በተቀሩ የትምህርት ዓይነቶች ላይ የመልስ ቁልፍ ችግር አለማጋጠሙ ተረጋግጧል። ነገር ግን በግለሰብ ደረጃ የቀረቡ ሁሉም አቤቱታዎች እየተጣሩ እንደተለመደው መልስ የሚሠጥ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

http://app.neaea.gov.et/?fbclid=IwAR1iqQIimiWDHoJvZvB1XVFXp6VnF55k8HZF7To6YUi0W8ISjFaa5SkNxxQ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *