የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና የፌዴራል ፖሊስ ሙስናን ለመከላከልና ለመዋጋት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ በሶስቱም ተቋማት መካከል የተፈረመዉ ሰነድ ተቋማቱ በመደጋገፍ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመዋጋት ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

እንዲሁም በሀገር ደረጃ የሚከናወነዉን የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ዉጤታማ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው በማመን የስምምነት ሰነዱ መዘጋጀቱ ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፌደራል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የመግባቢያ ሰነዱ እነዚህ ሶስት ተቋማት በህግ የተሰጣቸዉ ስልጣንና ሀላፊነት በመጠቀም የሚደረጉ ስርቆቶችና መሰል ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከልና ለመዋጋት ተባብረዉ የድርሻቸዉን በመወጣት የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡

እስከ ዛሬ የነበረዉን አሰራር ወደ ተቋማዊ ቅርፅ በማምጣት የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ እናምናለን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህጉ፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን የፌዴራል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉአለም ፣የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተኮላ አይፎክሩ ተፈራርመዋል፡፡

ፋና

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *