የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ስነ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል ስልጣን እንደሚጋሩ ነው የሚጠበቅ፡፡ ይህም በሀገሪቱ ለበርካታ ወራቶች የቆየውን የፀጥታች እና ህዝባዊ ተቃውሞ ፍፃሜ ያስገኛል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የልዑላዊ ምክር ቤት የሚቋቋም ሲሆን ምክር ቤቱ ስድስት የሲቪል እና አምስት ወታዳዊ አመራሮችን በአባልነት ያካታል፡፡

የልዑላዊ ምክር ቤቱን ሁለቱ ወገኖች በየሶስት ዓመት እየተፈራረቁ የሚመሩት ሲሆን በዚህ መሰረት ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የነፃነትና የለውጥ ሀይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚሾም ይሆናል፡፡

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በዚህ የመጨረሻ የስምምነት ስነ ስርዓት ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ሱዳን ካርቱም ገብተዋል።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ነሐሴ 11 ቀን 2011 ወደ ሱዳን ካርቱም በመጏዝ በወታደራዊ የሽግግር ሸንጎና በነፃነትና ለውጥ ኃይሎች መካከል የተደረገውን የመጨረሻውን የስምምነት ፊርማ ተከታተሉ:: ይህ የመጨረሻው ስምምነት ወታደራዊ ያልሆነ መንግስት ለመመስረት መንገድ ከፋች ነው::

ከስምምነት ፊርማው ቀደም ብሎ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከነፃነትና ለውጥ ኃይሎች አባላት ጋር ተወያይተዋል:: አባላቱ  ኢትዮጵያ ለዚህ ስምምነት መፈረም የተጫወተችውን ሚና በማድነቅ እነዚህ ሕገ መንግስታዊና ፖለቲካዊ ስምምነቶች ለዘላቂ ዴሞክራሲያዊና ልማት መሰረት ይጥላል ብለዋል::

ፋና


ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው ይቅርታንና አንድነትን በመንከባከብ እንዲተጉ በማበረታታት ስኬታማ ውይይት መልካም መነሻ እንጂ ብዙ ስራ የሚጠይቀው መንገድ ከዚህ ቀጣዩ ነው ብለዋል:: ሴቶች በፖለቲካ አመራር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ለዚህም አካታች እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል:: በተያያዘም የኢትዮጵያን ልምድ በማንሳት የነፃነትና የለውጥ ኃይሉ ይህንን 50-50 የፆታ አካይ
ታች ካቢኔ እንዲተገብሩ አስታውሰዋል::

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

በሱዳን ስምምነት ፊርማው ስነስርዓት በማስከተል ባደረጉት ንግግር ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በሀገሪቱ በሚደረገው የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ወቅት የሱዳን ህዝቦች የሰላማቸውና የክብራቸው ተንከባካቢዎች እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል::

በሱዳን ጉዞአቸው ማብቂያም ከመቶ በላይ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወደሌላ ሀገር ለመሻገር ሱዳን የቀሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ይዘው ተመልሰዋል:: ከነዚህም ውስጥ በተለያየ ጥፋት እስር ቤት የነበሩም ይገኙበታል::

#PMOEthiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *