እስራኤል በአሜሪካው ፕሬዚዳንት የዘረኝነት ጥቃት የተፈፀመባቸው እና እስራኤልን በተደጋጋሚ ሲከሱ የሚሰሙትን የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኢላን ኦማርና ራሺዳ ታሊብ ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች፡፡

ሁለቱ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት በቀጣዩ ሳምንት በእስራኤል ቁጥጥር ስር የሚገኙትን ዌስት ባንክ እና ምስራቃዊ እየሩሳሌምን ለመጎብኘት እቅድ ይዘው ነበር፡፡

እነዚህ ሴት የኮንግረስ አባላት አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቋርጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚደግፉ ሲሆን፥ የእስራኤል ህግ ደግሞ ዘመቻውን የሚደግፉ አካላት ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ይከለክላል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በትናንትናው ዕለትም በትዊተር ገፃቸው ወደ እስራኤል እንዲገቡ ከተፈቀደ ትልቅ ድክመት ነው ሲሉ አስፍረዋል፡፡

ትውልደ ሶማሊያዊቷ ኢላን ኦማር በበኩላቸው እስራኤል የዴሞክራሲ እሴቶች መጣሷን ጠቅሰው፥ ጉብኝቱን በተመለከተ ከአጋር መንግስት ለቀረበላት ጥያቄ አስደንጋጭ ምላሽ ሰጥታለች ብለዋል፡፡

ሁለቱን ሴቶች እስራኤል እንዳይገቡ ጥሪ ከማቅረባቸው በተጨማሪ እስራኤልና አይሁዶችን እንደሚጠሉ የገለፁት ትራምፕ ይህንን ሀሳብ መቀየራቸውን የሚያሳይ ነገር የለም ብለዋል፡፡

ነገር ግን የአሜሪካ ኮንግረስ አባላቱ ኢላን ኦማርና ራሺዳ ታሊብ እስራኤልን እና አይሁዳውያንን  እንደሚጠሉ የሚቀርብባቸውን ወቀሳ በተደጋጋሚ ያጣጥላሉ፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ – (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *