በተመደቡ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተንሰራፋውን ሌብነት መቆጣጠራቸውና ዝርፊያው እንዲቆም ከፍተኛ ስራ መስራታቸውን ህዝብ የሚመሰክርላቸው የቅዱስ ቁልቢ ገብርኤል ገዳም በመኖሪያ ክፍላቸው ሞተው ተገኝተዋል። ሕዝብ ቁጣውን ገልጿል። ጥይት ተተኩሶ ሰዎች ቆስለዋል። የስምንት ዓመት ታዳጊ ህይወት አልፏል።

የእኚህን አባት ድንገተኛ ሞት የሰሙ በሰላማዊ መንገድ መንግስት እንዲያጣራ ከያለበት ተጠራርቶ ጥያቄ አቅርቧል። መልዓክኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ከቅዳሴ መልስ በቤታቸው ሞተው መገኘታቸው ያስደነገጠው ህዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ካቀረበ በሁዋላ መንገድ በመዝጋት ትራንስፖርት ሊያስተጓጉሉ የሞከሩ በፈጠሩት ግርግር ተኩስ ተከፍቷል።

አቶ ኡመጥ በከሬ ሃራዋጫ የተወለዱና የጨለንቆ ከተማ ነዋሪ ናቸውል። በትራንስፖርት ዘርፍ ተሰማርተው ስለሚሰሩ በወቅቱ ቁልቢ ከተማ ነበሩ። ለዛጎል እንደተናገሩት ህዝብ ቁጣውን ሲገልጽ አይተዋል። የወረዳውን አስተዳደር ግድያው እንዲጣራና ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ህዝብ የጠየቀው በከፍተኛ ንዴትና ቁጣ ነበር። ይሁን እንጂ ለጥይት፣ ለረብሻና ለግድያ የሚያበቃ አንድም ነገር አላዩም።

Related stories   PM Abiy, U.S Senator Inhofe Hold Encouraging Conversation about Tigray

ዜናው እንደተሰማ በሚገርም ፍጥነት ከየአቅጣጫው የተሰባሰበው ሕዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ እያቀረበ ባለበት ሁኔታ መንገድ መዝጋት መጀመሩን የሚናገሩት አቶ ኡመጥ፣ ይህንኑ ተከትሎ መንገድ በሚዘጉትና በጸጥታ ሃይል መካከል ገጭት ተፈጠረ። ጥይተ ተተኮሰ። ዘግይተው እንደሰሙት ከቆሰሉት አምስት ሰዎች መካከል አነኛው ታዳጊ ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

ፖሊስ ሊታገስ ይችል እንደነበር ያመለከቱት አቶ ኡመጥ መንገድ መዝጋትና ሰላማዊ ተቃውሞን ወደ ሁከት መቀየሩም አግትባብ መስሎ እንደማይታያቸው ተናግረዋል።

Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

ለቪኦኤ ምስክርነታቸውን የሰጡ የቁልቢ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት  መልዓክኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ  በአስተዳዳሪነት ተሾመው ከመጡ ገና 4 ወራቸው ሲሆን፣ ከህዝቡ ጋርም ተቀራርበው የሚሰሩና በአጭር ጊዜ መዕመኑ የወደዳቸው አስተዳዳሪ ነበሩ። በአጭር ጊዜ የልማት መርሃ ግብር ዘርግተው መስራት የጀመሩና ቤተክርስቲያኒቱን ተብትቦ የያዛትን ሌብነት የማጽዳት ስራ እየሰሩ ነበር። ምስክሩ አያይዘው በጥይት ስለተጎዱት ሲናገሩ መንገድ መዝጋት የጀመሩ ሰዎች ድርጊተን ተከትሎ በተከፈተ ተኩስ መሆኑንን ጠቁመዋል።

ፖሊስም ሆነ የሚመለከተው አካል ግድያውን አስመልክቶ እስካሁን በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም። እናም መልዓክኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ማን ገደላቸው የሚለው ጉዳይ መልስ ይሻል። ጥይት ከፍተው ጉዳት ያደረሱም በህግ ሊጠየቁ ይገባል።

 

Related stories   በኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ ላይ የጸጥታው ምክር ቤት ሳይስማማ ተበተነ፤ አማራ ትህነግን በህግ ሊጠይቅ ነው

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *