ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ በዛሬው እለት ተፈራርመውታል፡፡

ከድጋፉ 95 ሚሊየን ፓውንዱ የፋይናንስ ተቋማትን ለማጠናከር፣ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና ለንጹህ ውሃ አቅርቦት እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ቀሪው 25 ሚሊየን ፓውንድ ለአራተኛው ዙር የሴፍቲኔት ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የውሃ ንጽህና አገልግሎት ድጋፉ ዓላማ በኢትዮጵያ በድርቅ በሚጠቁ አካባቢዎች የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ያህል ዜጎችን የንጽህና እና የንጽህና አጠባበቅ ልምድ ለማሻሻል ያለመ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ቀሪው 25 ሚሊየን ፓውንድ የሴፍቲኔት ድጋፍ በገጠር አካባቢዎች የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የምግብ ድጋፍ እና አደጋ ቅነሳ ስራ ለማከናወን የሚውል መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡

ኦቢኤን

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *