ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በየብስ የሚያገናኛትን ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አጠናቃ፣ በመጪው መስከረም 1 ቀን 2012 ዓ.ም እንደምታስመርቅ ተገልጿል፡፡

ባለፈው አመት ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረው የ90 ኪ.ሜትር የመንገድ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ መጠናቀቁን የዘገበው ኤርትሪያን ፕሬስ፤ ቀሪው 10 በመቶ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል ብሏል፡፡

ኤርትራን ከኢትዮጵያ በየብስ እንደሚያገናኝ የተነገረለት ይኼው መንገድ፤ ቀደም ሲል በ6 ሜትር ስፋት የተሰራ ሲሆን አሁን በተደረገው ማሻሻያና ተጨማሪ ግንባታ፣ በእጥፍ ጨምሮ፣ ከ12 እስከ 20 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጓል፤ 25 አዳዲስ ድልድዮችም ተገንብተዋል ተብሏል፡፡

በሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ ወሳኝ ሚና እንዳለው በሚነገርለት በዚህ የመንገድ ግንባታ ላይ በርብርብ የተሳተፉት 5 የኤርትራ የመንገድ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን ጨምሮ የአገሪቱ መከላከያ ሀይል መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ 
.
የመንገዱ እድሳትና ግንባታ አንድ አመት የፈጀ ሲሆን ሙሉ ወጭው በኤርትራ መንግስት መሸፈኑ ታውቋል፡፡

በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የመንገድ ግንባታው በአዲሱ ዓመት መስከረም 1 እንደሚመረቅና አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ኤርትሪያን ፕሬስ ዘግቧል፡፡

OBN

Related stories    ኬንያ ለመጀመርያ ጊዜ ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ውጭ ላካች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *