በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፈዲስ ወረዳ ለህግ የበላይነት መከበር እንቅፋት ሆነዋል የተባሉ 53 ተጠርጣሪዎችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዲቭዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፋ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ በወረዳው ቦኮ ከተማ ህብረተሰብን በመከፋፈል ለጸብ የሚያነሳሱ ተግባራትን  በተደጋጋሚ ሲፈጸሙ ቆይተዋል።

እንዲሁም ለደን ጭፍጨፋ የሚዳርጉ ግለሰቦችን ከማበረታታት ባለፈ በግለሰብና የመንግስት ንብረቶች ላይ ውድመትና ዘረፋ እንደፈጸም ሲነሳሱ እንደነበርም አመልክተዋል።

በወረዳው የሚገኙ ፍርድ ቤቶችና የፖሊስ ጽህፈት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዳያከናውኑ እንቅፋት እንደሆኑም ተጠቅሷል። እነዚህ 53 ተጠርጣሪዎች የተያዙት ከነሐሴ 18/2011ዓ.ም ጀምሮ ነው

እንደ ኮማንደር ስዩም ገለጻ በወረዳው የሚከከሰተውን የወንጀል ድርጊት ለመከላከል ነሐሴ 19 ቀን 2011 ዓ. ም በቦኮ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሰላም ኮንፍረንስ የተካሄደ ሲሆን የተያዙት ተጠርጣሪዎቹ የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኙም ተወስኗል።

በአካባቢው የሚታየውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት  በኮንፍረንሱ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች  ከፖሊስ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የወንጀል ድርጊቱ እንዲፈጸም ሲነሳሱና ሲያስተባብሩ  የነበሩት ተጠርጣሪዎች  በምርመራ የመለየት  ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ኮማንደር ስዩም አመልክተዋል።

ENA

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *