የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ስያሜ የሚጠራው የትግራይ ክልል ብቸኛ አስተዳዳሪ፣ በህዝብ ትግልና በደም በተከፈለ መስዋዕት ስልጣኑንን እንዲለቅ በተገደደ ማግስት ጓዙን ጠቅልሎ ወደ መቀሌ መግባቱና መመሸጉ ይታወሳል። ዛሬ እንደተሰማው ይህ ቡድን ተመልሶ አገር እንዲያስተዳድር ጥያቄ እንደቀረበለት በይፋ አስታውቋል።

ይህ አገርን በነጻ አውጪ ስም ላለፉት ለሃያ ሰባት ዓመታት ሲመራ የቆየ ሃይል ለውጡ በተረጋጋ መልኩ እንዳይቀጥል ሰፊ የፕሮፓጋንዳና በበጀት የተደገፈ የውክልና አገር ማተራመስ ስራ እንደሚሰራ በርካታ መረጃዎች ሲወጡ ቆይቷል። ይህ የማተራመስ ስራ ህዝብ ስለማ እንዳይሰማውና ስጋት ላይ እንዲወድቅ ማድረጉ ከተገመገመ በሁዋላ ነው ይህ ዜና የተሰማው። ዜናው ቃል በቃል እንዲህ ይነበባል።

ህወሃት በእህት ድርጅቶች በተፈጸመበት ክህደት ተጸጽቶ አገሪቱ እንድትፈርስ አሳልፎ በመስጠት ወደ መቀሌ መመለሱ ከባድ ስህተት መፈጸሙ ተገለጸ ሲል የትራይ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ አጭር ዜና አሰራጭቷል።

69249042_404612323500580_8165567900187361280_n.jpg

“በመሆኑም” ይላል ቢሮው ” በመሆኑም አጋጥሟት ካለው የመፈራረስና የመበታተን አደጋ ለማዳን ህወሃት ከሕዝብ ጋር በመናበብ በትግራይ የተፈጠረርውን ሰላም፣ ልማትና፣ በዛ በተፈጸመ እንዲያሰፍን ተጥይቋል” በሚል ህወሃት ለምን አገር የማዳን ጥያቄ እንደቀረበለት ያብራራል።

ከማንኛው የሕብረተሰብ ክፍል፣ ከእነማንና እንዴት፣ እንዲሁም በምን ዓይነት ውክልናና መድረክ ይህ እንደተጠየቀ ያላብራራው የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዜና ” ህወሃት በተፈጸመበት ክህደት ሳይደናበር ኢትዮጵያን ዳግም ለማዳን መስራት እንደሚገባው ጥሪ ቀርቦለታል” በማለት ዜናውን ይጨርሳል።

ዜናውን የሰሙ ወዲያውኑ በማህበራዊ ሚዲያ እንዳሉት ” የጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስት አስቸኳይ ምላሽ ሊሳጥ ይገባል” እያሉ ነው። አንድ ህጋዊ መንግስት ባለበት አገር ትግራይ ክልል አገር የማስተዳደር ስራ እንዲሰራ መጠየቁን በአደባባይ ይፋ ማድርጉና ይህንኑ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚተባበሩ ሁሉ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ በማደም ህግ ሊጠየቁ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

syum mesfine
Related stories   " ዴሞክራሲ ከህዝብ ሰላምና ከአገር አንድነት በላይ አይደለም " ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *