“የአማራ ህዝብ ከድህነት እንዲወጣ ቀን ከሌት የሰራን ምንም ጥፋት የለብንም የወንጀል ማቅለያም አናቀርብም”

ዛሬ ያስችለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእሥር ላይ የሚገኙትን የብአዴንና የአህአዴግ የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳን በተከሰሱበት የሙስና ወንጅል ጥፋተኛ ናቸው ሲል በየነ። በአባሪ ተባባሪነት ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት አቶ ዳንኤል ግዛው ግን ጥፋተኛ አይደሉም ሲል ወስኗል።አቶ በረከት እና አቶ ታደሰ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ላለፈው አንድ አመት ከ4 ወር በአማራ ክልል በፍርድ ቤት ሲከራከሩ ቆይተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ በረከት ከተከሰሱባቸው4  ክሶች መካከል በሁለቱ ጥፋጠኛ ናቸው ሲል ነው ዛሬ የበየነው።እነርሱም ከዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር ሽያጭ  ጋር በተያያዘ አንድ ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር እንዲባክን አድርገዋል፣የሚለው እና ከጁቬንቱስ  ዊንግ ኩባንያ ጋር በተደረገ ውል የጥረት ኮርፖሬት ፣210 ሚሊዮን ብር እንዲባክን አድርገዋል የሚሉት ሁለት ክሶች ናቸው።

Related stories   " አሜሪካ ስለ ዴሞክራሲ፣ ጸጥታና ደህንነት የማውራት ሞራል የላትም፤ የአገራችን ሚዲያዎች ያሳዝናል"

አቶ ታደሰ ካሰም አቶ በረከት ጥፋተኛ በተባሉባቸው ሁለቱ ክስችና  በ4ኛ ክስ ለጁቨንቱስ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የጥረት ኮርፖሬሽንን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ “ኮርፖሬት ጋራንቲ” በመስጠት ጥፋተኛ ተብለዋል።3ኛው ክስ ለጁቬነቱስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ድርጅት አግባብ ያልሆነ ዋስትና መስጠት የሚል ነው።አቶ ዳንኤል ግዛው በተከሰሱባቸው 3ኛና 4ኛ  ክሶች ነፃ መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል።

ጥፋተኛ የተባሉት አቶ በረከት ስምዖን የጥረት ኮርፖሬት ቦርድ ሰብሳቢ፣ አቶ ታደሰ ካሳ ደግሞ ዋና ሥራ አሰፈፃሚ ነበሩ።ሁለቱም “የአማራ ህዝብ ከድህነት እንዲወጣ ቀን ከሌት የሰራን ምንም ጥፋት የለብንም የወንጀል ማቅለያም አናቀርብም” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።ሆኖም ፍርደ ቤቱ ተከሳሾች የህግ ባለሙያ አማክረው የወንጀል ማቅለያ እንዲያቀርቡ ለሚያዝያ 28/2012 ቀጠሮ መስጠቱን የባህርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ዘግቧል።

DW

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *