ዛሬ በኢትዮጵያ የግል ቴሌቪዥኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው። ችግሩን መቋቋም አቅቷቸው የተዘጉም አሉ። በአብዛኛው የጠላና አልኮል ማስታወቂያ ተሸክሟቸው የነበሩ የቴሌቪዥን ተቋማት ማስታወቂያውን የሚያቅብና ህግ ከወጣ በሁዋላ መንኮታኮታቸውን በአዲስ አበባ በሙያው የተሰማሩ እየገለጹ ነው።

ስም መዘረዘሩ አስፈላጊ ባይሆንም ሰራተኛ የበተኑ፣ የቀነሱ፣ ከነ አካቴውም ያቆሙ አሉ። በተመሳሳይ በዘርፉ ለመሰማራት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አዳዲስ ነጋዴዎችም ለጊዜው ራሳቸውን ተመልካች ማድረግ መርጠዋ።

ወደ ሳተላይት ለመውጣት ቃል ገብተውና ማስታወቂያ አስለፍፈው የነበሩ አንድም ማስታወቂያ ባማስነገር፣ አለያም ሃሳባቸውን ለጊዜው በመግታት የዩቲዩብ ምሽግ ውስጥ ሆነው በተልመካች ብዛት የሚገኘውን ገቢ እየተቋደሱ ናቸው። እስከመቼም በዚሁ መንገድ እንደሚዘልቁና የራሳቸውን ወጥ ስራ ለተመልካች የማቅረብ አቅማቸውን እንደሚያሳድጉ ፍንጭ አይታይም። የዲሲ ነዋሪ ለዛጎል እንዳለው የዩቲዩብ ገቢ ባለሙያ አሰማርቶ ሙያው የሚጠይቀውን ሁሉ ለማድረግ ስለማይቻል የመንግስት ሚዲያዎችና ማህበራዊ ገጾችን ምንጭ በማድረግ፣ በመቅዳትና በማሰራጨት አሁን እንደሚታየው ከማዝገም ውጪ አማራጭ የለም።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ይኸው አስተያየት ሰጪ እንደሚለው አሁን የሚስተዋለው አካሄድ ሙሉ ለሙሉም ባይባለም ባብዛኛው ” ገበያ ተኮር ወይም ክሊክ ተኮር” በመሆኑ አርእስት በማስጮህ፣ ባብዛኛው ለአሉባልታ ማናፈሻ ፣ የርስ በርስ መላተሚያና የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሲያልፍም ለገቢ ሲባል ድርጅቶችንና ግለሰቦችን መደብደቢያ ሆኗል። በዚህ ባህሪው መቀጠል ስለማይችል የዩቲዩብ ገበያውም በሂደት ተመሳሳይ ችግር እንደሚገጥመው ይገምታል።

በተመሳሳይ የጋዜጣ ወይም የህትመት ሚዲያዎችም ወደ ኦንላይን ገበያ ማምራታቸው አይቀርም። በአዲስ አበባ የዘርፉ ባለሙያ በማህበራዊ ገጹ ላይ እንዳለው የሕትመት ውጤቶች ቀደም ሲል ጀመሮ በህትመት ዋጋ ንረት ደብዛቸው ጠፍቷል። ያሉትም ቢሆኑ በማስታወቂያ እየተደጎሙ እንጂ የጋዜጣ ሽያጭ የሚያካሂዱት በኪሳራ ነው። አሁን ደግሞ ማስታወቂያውም በወረርሽኙ ምክንያት እየቀነሰ በኪሳራ ማሳተሙ አዳጋች የሆነበት ወቅት ነው። በዚህ መልኩ መቀጠልም አይቻልም።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ሰብለ ዮሃንስ በአገር ውስጥ የሚታተሙ የህትመት ስራዎች ወደ ኦንላይን ገበያ ካመሩ አሁን ባላቸው ይዘት ተፎካካሪ አይሆኑም። ሰብስክራይበርም በሚፈልጉት መጠን አያገኙም ባይ ናት። ስታስረዳ ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሁሉንም ጉዳይ በየደቂቃው ይዘግባሉ። ተቋማትና ባለስልጣናት መረጃ በማህበራዊ ገጻቸው ያስተላልፋሉ። ዛሬ ምንጭ ተብለው የሚጠቀሱት የባለስልጣናትና የተለያዩ ተቋማት የማህበራዊ ገጾችና የመንግስት ሚዲያዎች ናቸው። በዚህ መነሻ እነዚህን መረጃዎች ደግሞ በማተም ሰብስክራይብ የሚያደርግ አካል ይኖራል ብሎ በጉጉት መጠበቁ አግባብ አይሆንም።

የንግድና ስትራቴጂ ባለሙያ መሆኗን የምትናገረው ሰብለ፣ ሚዲያዎች ወደ ኦንላይን ቢዝነስ ከገቡ ሊነበቡ የሚችሉ፣ ወይም ሊሰሙ የሚችሉ የራሳቸው የሆነ ወጥና ጥልቅ ስራ በየዘርፉ ማዘጋጀት አለባቸው። ይህ ደግሞ ብቃትንና እውቀትን ይጠይቃል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

በውጭ አገር በገንዘብ የሚሸጡ ታሪኮች፣ የምርመራ ሪፖርቶች፣ መረጃዎችና የባለሙያዎች ትንታኔ ለለመደው ህዝብ ከመንግስት ሚዲያና የባለስልጣናት የመረጃ መረብ ወይም ማህበራዊ ገጾች ላይ እየገለበጡ ቀን በመጠበቅ ማተም አዋጪ እንደማይሆን ሰብለ ታሳስባለች። አታሚዎች ይህንን አስቀድመው ሊያስቡበት እንደሚገባም ትመክራለች።

በውጪው ዓለም ማን አንባቢ፣ አምን የዩቲዩብ ወሬ ተከታትይና የማህበራዊ ሚዲያ ምርት አፋሽ እንደሆነ ለማወቅ አሉባልታ የሚናፈስባቸውን ገጾች፣ የገጹን ባለቤቶችና፣ የሚተላለፈውን ወሬ በማየት ስንት ተከታይ እንዳላቸው ማስላት በቂ ነው። ሰብለ እንደምትለው ዲጂታል ሚዲያው ምን ያህል ስራና ጥረት፣ እንዲሁም መረጃን በቅጽበት ውስጥ የማዳረስ የጊዜ ሩጫው ቀላል አይሆንም።

በአገር ውስጥ ደግሞ የኢንተርኔት ጥራትና ፍጥነትም እንዲሁ በትልቁ ግምት ውስጥ የሚገባ ነው!!Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *