የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ በረከት ስሞኦን የስድስት እንዲሁም በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ደግሞ የስምንት ዓመት የእስር ፍርድ ወሰነ።

ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የቅጣት ማክበጃ እና ተከሳሾች ያቀረቧቸውን የቅጣት ማቅለያዎች ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም ተከሳሾች በጠበቃቸው በኩል በቅጣት ማቅለያነት ያቀረቧቸውን የቤተሰብ አባል መሆናቸው፣ ህመምተኛ መሆናቸው እና ከዚህ በፊት ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት አለመፈፀማቸውን በቅጣት ማቅለያነት ፍርድ ቤቱ ይዞላቸዋል።

Related stories   እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር - ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

በተጨማሪም ለበርካታ አመታት በመንግስትና የፖለቲካ ስራ መስራታቸው በማቅለያነት ተይዞላቸዋል።

ፍርድ ቤቱ በዓቃቤ ህግ በኩል ተከሳሾች በመንግሥትና በፖለቲካ ስራ ማገልገላቸው ህጉን ከሌላው ሰው የበለጠ እንዲያውቁት የሚደርግ በመሆኑና ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ሊጠየቁ ይገባል ሲል ያቀረበውን ማክበጃ አልተቀበለውም።

ፍርድ ቤቱም ከላይ የተነሱትን የቅጣት የማቅለያና ማክበጃ መሰረት አድርጎ ተከሳሾች ሀላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት፥ አቶ በረከት ስምኦን በሁለት ክሶች እንዲሁም አቶ ታደሰ ካሳ በሶስት ክሶች ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል።

Related stories   PM Abiy, U.S Senator Inhofe Hold Encouraging Conversation about Tigray

በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቶ አቶ በረከት ስምኦን በስድስት አመት እስራትና 10 ሺህ ብር እንዲሁም አቶ ታደሰ ካሳ ደግሞ በስምንት አመት እስራትና 15 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።

በናትናኤል ጥጋቡ –  (ኤፍ ቢ ሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *