በነጆ አራት የመንግሥት ሰራተኞችን የረሸኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ለመያዝ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ሰባቱ ሲገደሉ፤ ሦስቱ እጃቸውን ሰጡ

” በርካቶች አምንስቲን ቀለም አምላኪ ነጮች፣ የኒዎ ኮሎኒያል ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ያለ ክብሩና ያለ ንጽህናው በማወደስ፣ በማሞገስና ተደማጭነት እንዲኖረው በማድረግ፤ ዓላማቸውን እንዲያሳካ የሚያሰማሩት ለስላሳ ሃይል (Soft Power) ነው ። ይህ ብቻ አይደለም፣ አምንስቲ የገዢዎቹን ተልዕኮ ማስፈጸሙ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በተረፈው ሰዓት፣ ጊዜና እግረ መንገዱን የራሱን “ጥሪ” እና “ተልዕኮ” አንግቦ፣ የበለጠ ለቀረበውና ለከፈለው የሚተጋ የመፈንቅለ መንግስትና የብሔር ግጭት ሴራ መጠንሰሻና መቀፍቀፊያ ተቋም እንደሆነ በርካቶች የሚያሰማሙበት ነው” ሲሉ አቶ ሞሼ ሰሙ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል

ሲሸፋፋን የቆየው የኦነግ ሸኔና የመንግስት መካሰስ ይፋ እየሆነ ነው። አምነስቲ አወጣው የተባለውን ሁሉንም ወገን ያላካተተ ሪፖርት ተከትሎ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ደብቆ የያዘውን መረጃ ይፋ ማድረግ ጀመረ።

Related stories   መንግሥት ቢቢሲና ሮይተርስን ጨምሮ ሰባት ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ትግራይ ክልል ገብተው እንዲዘግቡ ተፈቀደ

የኦሮሚያ አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ በምዕራብ ኦሮሚያ በተለያዩ ዞኖች በኦነግ ሸኔ በፈጸመው ጥቃት ከ770 በላይ ሰዎች እንደገደለና ከ1300 በላይ በሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ነው ያስታወቀው።

72 ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ያመለከተው የቢሮው ሃላፊ መግለጫ መልዕክቱ አምነስቲ ይህንን ሁሉ ጉድ ስለምን በሪፖርቱ አላካተተም ለሚለው ምላሽ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዶክተር ዳንኤል በቀለ ዛሬ ማለዳ ለሸገር እንዳሉት የአምነስቲን ሪፖርት ተቀብሎ ማጣራት የምንግስት አግባብነት የተሞላው ተግባር መሆኑን ገልጸው፣ ሪፖርቱ ተፈጸመ ያለውን ጉዳይ ከተፈጸመ በምንና እንዴት ባለ አግባብ ሊፈጸም ቻለ የሚለውን ጉዳይ እንዳላጤነው በይፋ አመላክተዋል።

Related stories   የአምነስቲ " ሽንቁረ ብዙ" ሪፖርት የተከፋዮች የቲውተር ዜና ድምር

ሌላ በዘርፉ የሚሰሩ እንዳሉት ሪፖርቱ በአምነስቲ ደረጃ የተዘጋጀ አንደማይመስላቸው ገልጸው መንግስት እስከሚቻለው እርቀት በሜድ ሊያጋልጣቸው እንደሚገባ፣ ምሁራንም ይህንን አካሄድ በመደገፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ሪፓርቱን ጠለቅ ብለን ስንፈትሽ ግን የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት አንድ ክልልን፣ ያውም አንድ የፖለቲካ መስመርን ብቻ ተከትሎ ለምን ተዘገበ የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድደናል። ከታሪክና ከተሞክሮ እንደምንረዳው። አምንስቲ በአንግሎ ሳክሰን ነጮች የተሞላ፣ በግልጽ ከሚዘግበው ባልተናነሰ የሕቡዕ ዓላማና ግብ የተበጀለት ከምዕራብውያን ውጭ ሌላው የዓለም ፍጡር ሁላ ግፈኛና አረመኔ አስመስሎ ለማሳየት የተመሰረተ ተቋም ነው። የሚሉት አቶ ሞሼ ሰሙ በጥልቅ ነቀፌታቸውን አሰምተዋል።

” በርካቶች አምንስቲን ቀለም አምላኪ ነጮች፣ የኒዎ ኮሎኒያል ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ያለ ክብሩና ያለ ንጽህናው በማወደስ፣ በማሞገስና ተደማጭነት እንዲኖረው በማድረግ፤ ዓላማቸውን እንዲያሳካ የሚያሰማሩት ለስላሳ ሃይል (Soft Power) ነው ። ይህ ብቻ አይደለም፣ አምንስቲ የገዢዎቹን ተልዕኮ ማስፈጸሙ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በተረፈው ሰዓት፣ ጊዜና እግረ መንገዱን የራሱን “ጥሪ” እና “ተልዕኮ” አንግቦ፣ የበለጠ ለቀረበውና ለከፈለው የሚተጋ የመፈንቅለ መንግስትና የብሔር ግጭት ሴራ መጠንሰሻና መቀፍቀፊያ ተቋም እንደሆነ በርካቶች የሚያሰማሙበት ነው” ሲሉ አቶ ሞሼ ሰሙ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል። እዚህ ላይ ሙሉውን ያንብቡ

Related stories   WAR, JUSTIFIABLE WAR? "ጦርነት ለሃገር ህልውና" by Dr. Haymanot

በሌላ ዜና በነጆ አራት የመንግሥት ሰራተኞችን የረሸኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ለመያዝ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ሰባቱ ሲገደሉ፤ ሦስቱ እጃቸውን መስጠታቸው ታውቋል። እነዚህ ለጋ ምልምሎች የሲቪል ሰራተኞችን ረሽነው ብዙም ሳይርቁ የመከላከያ ሰራዊት አሳዶ እጅ እንዲሰጡ ቢጠይቅም ፈቃደኛ ባለመሆን ተኩስ በመክፈታቸው ሰባቱ ወዲያው ተደምስሰዋል። ሶስቱ እጅ ለመስተት ተገደዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *