በዛሬው ቀን ብቻ 141 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን ዶክተር ሊያ ይፋ አድርገዋል። በሁሉም መስክ ነገሮች ወደ ውስብሰብ ችግር የማምራታቸው ጉዳይ እውነት እየሆነ ነው። እውነት ደግሞ እውነት ነው። ኑሮ፣ ችግር፣ ወረሽኙን ተከትሎ የሚመጣው ጣጣ ሳያንስ ወገን ወገኑንን መግደልም ታክሎበታል። ለወንበር ሲባል ህዝብ ተዘንግቷል። የሚሰሩትን እንዳይሰሩ መወጥርም አጀንዳ ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 141 የላብራቶሪ ምርመራ 150 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 1 ሺህ 637 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት እለታዊ ሪፖርት ገልፀዋል።

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 147 ሰዎች ኢትዮጵያውያን፤ 3 ደግሞ የውጭ ዜጎች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ3 እስከ 72 ዓመት የሆኑ 94 ወንዶችና 56 ሴቶች ናቸው።

ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 123 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ 1 ሰው ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ትግራይ ክልል፣ 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ኦሮሚያ ክልል፣ 13 ሰዎች አማራ ክልል እንዲሁም 6 ሰዎች ሶማሌ ክልል ናቸው።

በሌላ መልኩ 4 ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 250 ደርሷል።

Related stories   የኮቪድ ጽኑ ታማሚዎች ቁጥር መብዛቱ በዲላ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና አስከትሏል

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ 18 የደረሰ ሲሆን፥ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ተመኝተዋል።

በ 24 ሰዓታት ውስጥ የተደረጉ የላቦራቶሪ ምርመራ ናሙናዎቹ ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወድስ የተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል።

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ125 ሺህ 570 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 636 ደርሷል።

አሁን ላይ 1 ሺህ 366 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፥ እስካሁንም 250 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፤ የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው ጃፓን መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *