አብን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርቦ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ለመንግስት ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ የአማራ ክልል ቀደም ሲል ከሚለው ባለፈ “ትህነግ የቅማንት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን አስታጥቋል” በሚል ላቀረበው ክስ፣ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለሰጠው ይፋዊ መግለጫ ምላሽ ሰጠ።

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽንስ ቢሮ ትናንት ይህን ያለው የአማራ ክልል ባለስልጣናት በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ቀርበው ትህነግ የቅማንት ተዋጊዎችን አስታጥቋል  ሲሉ በገሃድ ላቀረቡት ማስተባበያ ሲሰጥ ነው ።

የቅማንት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን አስታጥቋል መባሉ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግፋቸውን ለመሸፈን ሶስተኛ ወገን ላይ ጣታቸውን ለመጠቆም ያደረጉት ስልት መሆኑን በማስታወቅ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ መሆኑን አመላክቷል።

“የሶስተኛ ወገን ልክፍት፤ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” በሚል ርዕስ የተሰራጨው መግለጫ ትህነግ በምዕራብ ኢትዮጵያ ወለጋ ራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር ሆኖ የኢትዮጵያ መንግሥትን ይወጋል መባሉንም እንደማይቀበለው የገለጸው በማጣታል ነው።

ትህነግ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የሚታገል የፖለቲካ ፓርቲ መሆኑን ያመለከተው መግለጫ፣ ሰላዊ ፓርቲ “ሰራዊት ሊኖረው አይችልም፤ ክሱ ይሉኝታ የጎደለው የሚዲያ ልፈፋ ነው” በማለት ተቃውሟል።

የኦሮምያ ክልል ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ህወሃት ከአማጺ ቡድን ጋር ታጥቆ እየተዋጋ ነው ሲል መወንጀሉ ይታወሳል። የኦሮሚያ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ትህነግ ሲያሰለጥናቸው የነበሩና አምልጠው በመምጣት እጃቸውን የሰጡ ምስክሮች አሉ። ከዚህም በተጨማሪ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ በተካሄደው ኦፕሬሽን በርካቶች መማረካቸውን በገደምዳሜ ይፋ አድርገዋል።

የአማራም ሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግስታት ትህነግን በገሃድ ከትጥቅ ትግል ጋር በማያያዝ ውስጥ ውስጡን ሲነገር የነበረውን አደባባይ ማውጣታቸው አብን ለመንግስት ካቀረበው ጥያቄ ጋር ይገናኝ አይገናኝ የታወቀ ነገር የለም። ትህነግ በዓለም አቀፍ ደረጃ እስካሁን ድረስ በአሸባሪነት መዝገብ ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወሳል።

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *