የኮሮና ቫይረስ በዓለማችን ላይ ከተከሰተ ወዲህ በዓለማችን ላይ ከ7 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወትም ቀጥፏል።

ቫይረሱ በዓለማችን ላይ ከተከሰተ ወዲህ የተለያዩ የዓለም ሀገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ እና ለመከላከል በርካታ እርምጃዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል።

ከተወሰዱ እርምጃዎች ውስጥም ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ የሚከለክለው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለው “ቤት ውስጥ የሞቆየት ፖሊሲ” አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

Related stories   ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ታዲያ ከሰሞኑ የተሰራው ጥናትም ጥብቅ ከቤት ያለመውጣት ወይም የእንቅስቃሴ ገደብ በጣሉ 11 የአውሮፓ ሀገራት ላይ ሊከሰት ይችል የነበረን ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሞት ማስቀረቱን አመላክቷል።

በብሪታኒያዋ ለንደን በሚገኘው እና በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሀገሪቱን መንግስት የሚያማክረው ኢምፔሪያል ኮሌጅ ያጠናው ጥናት እንደሚያመላክተው፥ ሀገራት ዜጎች ከቤታቸው እንዳይወጡ የጣሉት ክልከላ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በአጭር ጊዜ እንዲከላከሉት አስችሏል።

Related stories   ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ብሪታኒያ፣ ስፔን፣ ቤልጂየም፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን እና ስዊዘርላንድ ያስተላለፉት  በቤት ውስጥ የመቆየት ፖሊሲዎች በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት ይከሰት የነበረን 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ገደማ ሞት መከላከል እንደቻለም ጥናቱ አመላክቷል።

ሀገራቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ እነዚህን እርምጃዎችን ባይወስዱ ኖሮም እስከ ባለፈው ግንቦት ወር ብቻ በቫርሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ12 ሚሊየን እስከ 15 ሚሊየን ሊደርስ ይችል እንደነበረም ጥናቱ አመላክቷል።

Related stories   ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ምንጭ፦ aljazeera.com ፋና

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *