ባለፉት 24 ሰዓታት ለ6 ሺህ 187 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 170 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ከዚህ ውስጥ 93 ወንድ እና 77 ሴቶች ሲሆኑ፥ ከ2 እስከ 115 የእድሜ ክልል የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
 81 አዲስ አበባ፣ 57 ሶማሌ ክልል፣ 13 አማራ ክልል፣ 7 ትግራይ ክልል፣ 7 ኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሐረሪ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች ከደቡብብ ክልል ናቸው።
 በትናንትናው እለት 22 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 401 አድርሶታል። በሌላ በኩል 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፥ በአጠቃላይ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *