ዱንያ መኮንን ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገች የሕግ ባለሙያ ናት። በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘችው ኢትዮጵያ ሲሆን በተባበሩት መንግሥታትና መንግሥታዊ ባልሆኑም ድርጅቶች ውስጥ በሰብዓዊ መብት ባለሙያነቷ አገልግላለች። በሥራ ዓለም ከተሠማራችበት ጊዜ አንስቶ ትኩረቷን በሴቶችና በሕፃናት መብት ጥሰት ዙሪያ ላይ በማድረግ ሠርታለች።
በሴቶች ላይ በሚደረጉ የመብት ጥሰቶች ላይ በኢትዮጵያም ትሠራ እንደነበር የምትናገረው ዱንያ፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ውስጥ የነፃ ሕግ አገልግሎት ትሰጥ ነበር።
በወቅቱ በአገሪቱ ለሴቶች መብት ጥሰት እምብዛም ትኩረት ስላልነበረና ጥቃቶቹም በብዛትና በተደጋጋሚ ያጋጥሙ ስለነበር በይመለከተኛል ስሜትና የሕግን ሚና በማስተዋል ሥራውን ለመቀላቀል መገፋፋቷን ታስረዳለች።
ዱንያ በተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ክፍል ውስጥ በሴቶች ጥቃት ላይ አተኩራ ትሠራ በነበረበት ወቅት በደረሰችባቸው ግኝቶች ምክንያት ሥራው በይበልጥ ትኩረት እንደሚያስፈልገው ተረዳች። read the full story on BBC
በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ41 ሺህ አልፏል
በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። አሁን ላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከብሪታንያ በመብለጥ ከ41 ሺህ አልፏል። አሃዙ ከአሜሪካ ቀጥሎ ዓለም ላይ ሁለተኛው ሆኗል።
አሁን ላይ በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ 828 ሺህ 810 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው፥ ወደ 42 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።
ይሁን እንጅ በሃገሪቱ ካለው የመመርመር አቅም ውስንነት አንጻር ቫይረሱ በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት ከተነገረው ይልቅ ከፍተኛ መሆኑንም ነው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች የሚያመላክቱት።
ከዚህ ባለፈም የቫይረሱ ስርጭት በቀጣዮቹ ሳምንታት “ከፍተኛ” የሚባል ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል ከመባሉ ጋር ተያይዞ ቀጣዮቹ ሳምንታት ለሃገሪቱ ፈታኝ ናቸው እየተባሉ ነው።
የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ከቫይረሱ ይልቅ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት በተጎዳው ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት ማድረጋቸው እየተነገረ ነው።
ይህ መሆኑ ደግሞ ለቫይረሱ ስርጭት “ግድ የላቸውም” በሚል ወቀሳው እና ትችቱ በርትቶባቸዋል።
—————————————————————————————————————–